Saturday, 02 June 2018 11:09

Infe ction (መመረዝ) በእርግዝና ወቅት…

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)


    ከእርግዝና ጋር በተገናኘ የሚከሰት መመረዝ (Infection) እና ከእናት ወደልጅ መተላለፉን በተመለከተ ባለፈው እትም በእርግዝና ጊዜ የበሽታ መቋቋም ኃይል እንዴት እንደሚቀንስ፤ በእርግዝና ጊዜ የሰውነት ተፈጥሮአዊ ለውጥ እንደሚኖር፤ በዚህም ሳቢያ በእናትየው ላይ እና እንዲሁም በልጁ ላይ የሚደርሱ ችግሮች ምን እንደሆኑ የሚያሳዩ ነጥቦች ተዘርዝረዋል፡፡ በዚህ እትም ደግሞ በእርግዝና ጊዜ እናትየውን ለበሽታ infection የሚዳርጉ ምክንያቶችና ለተረገዘው ልጅም በምን መንገድ ጠንቅ ሊሆኑ እንደሚችሉ የሚያሳየውን የተወሰኑትን ምክንያቶች ታነቡ ዘንድ እነሆ፡፡
የሰው ልጅ በሕይወት ዘመኑ ብዙ ቫይረሶችና ባክቴሪያ ሊያጋጥመው ይችላል፡፡ ነገር ግን በተፈጥሮው በሽታን የመቋቋም ኃይል ስላለው እነዚህን ለ infection (መመረዝ) የሚያበቁትን ቫይረሶችና ባክቴሪያ በመከላከል ሊያስወግዳቸው ወይንም ሊቋቋማቸው ይችላል፡፡ በእርግዝና ጊዜ ሁኔታዎችን ለየት የሚያደርገው እርግዝናው የበሽታ መከላከል ኃይልን ሊቀንስ እና በሰውነት ላይ በሚደርሰው ተፈጥሮአዊ ለውጥ የተነሳ ለበሽታ ለመጋለጥ ቀላል መሆኑ ነው ፡፡ሰለዚህም ለ infection (መመረዝ) የሚያበቁት ምክንያቶች ምንድናቸው ? መፍትሔውስ ?የሚለው ሁሉ ንም ሳይሆን በመጠኑ በዚህ እትም ተገልጾአል፡፡
ጉድፍ፡-
ጉድፍ የተሰኘው ሕመም እርጉዝ ሴቶችን ለ infection መመረዝ ከሚያበቁ በሽታዎች አንዱ ነው፡፡ ይህ ቫይረስ ለእናትየው ብቻም ሳይሆን ለአረገዘችውም ልጅ የመተላለፍ እድሉ ሰፊ በመሆኑ በፍጥነት ወደሕክምናው መሔድ ተገቢ ነው፡፡ በእርግጥ ወደ 95% የሚሆኑ እናቶች ይህ ቫይረስ ላይይዛቸው ይችላል፡፡ ወይንም አስቀድሞም ከያዛቸው በድጋሚ ላይከሰት ይችላል፡፡ ነገር ግን አንዲት እርጉዝ ሴት ይህ ሕመም ሊይዛት የምትችል ከሆነች ከያዛቸው ሕጻናትም ይሁን ትልልቅ ሰዎች ጋር በቅርበት ስትሆን በፍጥነት ወደሐኪም በመሔድ ሁኔታውን ማማከር ይጠቅማል፡፡
infection (መመረዝ) በተለይም ተረግዘው ላሉ ሕጻናት እጅግ አደገኛ የሚባል ሕመም ነው፡፡ infection ካረገዘችው እናት ወደልጅ ከተላለፈ በልጁ ላይ የመስማት ችሎታን የማሳጣት፤ ማየት እንዲሳነው ማድረግ ፤ የሚጥል በሽታ እንዲይዘው ወይንም ለትምህርት በሚደርስበት ጊዜ ትምህርቱን በአግባቡ የመቀበል ችግር እንዲገጥመው ሊያደርግ ይችላል፡፡ ምንም እንኩዋን ሁልጊዜ ችግሩን አስቀድሞ ለመከላከል ይቻላል ባይባልም በተቻለ መጠን ግን ለመከላከል ለቅድመ ጥንቃቄው የሚከተሉት ነጥቦች ተጠቅሰዋል፡፡
በማንኛውም ሰአት በተለይም በባዶ እጅ ወይንም በሶፍት አንዳንድ ጽዳቶችን ካደረጉ ወይንም በሕጻናት ማቆያ ውስጥ የሚሰሩ ከሆነ እጅን በሳሙናና በሞቀ ውሀ መታጠብ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡
ሕጻናትን ፊታቸውን መሳም ተገቢ አይደለም፡፡ ባይሆን ወደ እግራቸው አካባቢ መሳም ይቻላል፡፡
በአንድ ብርጭቆ በጋራ መጠጣት ወይንም ምግብን ከሕጻናት ጋር መጋራት አግባብ አይደለም፡፡
እነዚህ ማሳሰቢያዎች የሚያስፈልጉት በተለይም ከሕጻናቱ ጋር በጣም በቅርበት የሚገናኙ ከሆነ ነው። በተለይም በእርግዝና ወቅት የደም ምርመራ በማድረግ አስቀድሞውኑ በቫይረሱ ተመር ዘው እንደሆነና እንዳልሆነ ማረጋገጥ ይገባል፡፡
ሌላው ሕመም  በባክቴሪያ አማካኝነት የሚመጣው በሳይንሳዊ ቃሉ Group B strepto- coccus(GBS) የሚባለው ነው፡፡ ይህ እስከ 30% በሚሆኑ ሰዎች ላይ የሚገኝ ሲሆን በተለይም በሴቶች አንጀትና ብልት አካባቢ ብዙ ጊዜ ሊኖር ይችላል፡፡ ይህ ባክቴሪያ በተለይም ከእናቶቹ ይልቅ ለተረገዙት ልጆች ጤና ጠንቅ ነው፡፡ ልጆቹን የሚመርዛቸውም ከምጥ በፊት ወይንም በምጥ ጊዜ ሲሆን ሕመሙም ከፍተኛ ነው፡፡ ስለዚህም እናትየው ይህ ቫይረስ እንዳለባት ከታ ወቀ የበሽታ መከላከያ የሆኑ መድሀኒቶችን በመውለድ ጊዜ እንድትጠቀምና አደጋውን ለመቀነስ መሞከር ይጠቅማል፡፡ በእርግዝና ወቅት በሽንት ቧንቧ አካባቢ ይህ መመረዝ እንደነበረ ከታወቀ ህጻናቱ በተወለዱ ጊዜ መድሀኒቱን መስጠት ያስፈልጋል፡፡
(GBS) ሕጻናቱን በይበልጥ ሊይዛቸው የሚችለው፡-
ከ37/ሳምንት በፊት ቀኑ ሳይደርስ ምጥ ከመጣ፤
የሽርት ውሀ አስቀድሞ ካለቀ፤
በምጥ ሰአት ከፍተኛ ትኩሳት ካለ፤
ልጁ በመወለድ ላይ በሚኖርበት ወቅት እናትየው (GBS) ካለባት፤
በእርግጥ ይህ ባክቴሪያ መኖር አለመኖሩን የህክምና ባለሙያዎቹ በምርመራ ስለሚያውቁ የሚወለደውን ልጅ ደህንነት ለመጠበቅ ሲሉ አስቀድመው ምን መደረግ እንዳለበት ይወስናሉ፡፡
በእንስሳት አማካኝነትም Infections መመረዞች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ የተወሰኑትን እናስነብባችሁ፡-
ድመት፡-
የድመቶች ካካ ለልጆች እጅግ አደገኛ እና ጎጂ የሆነ Infection ሊያስከትል ይችላል፡፡ ይህንን ችግር ለማስወገድ በተለይም እርጉዝ ሴቶች፤
ድመቶች የሚተኙበት ወይንም የሚመገቡበትን እቃ እና አካባቢያቸውን ለማጽዳት መሞከር የለባቸውም፡፡ምናልባት ይህንን የሚሰራ ሰው በቤት ውስጥ እንኩዋን ባይኖር እጅን በጉዋንት በመሸፈን ተገቢውን የጽዳት መጠበቂያ በመጠቀም በየቀኑ ማጽዳትና በተለይም የሚመገቡበትን እቃ ከአጠቡ በሁዋላ ለአምስት ደቂቃ ያህል በፈላ ውሀ መሙላት ያስፈልጋል፡፡ ድመቶቹ የሚጠቀሙበትን እቃም ሆነ አካባቢ በእጃቸው መንካት የለባቸውም፡፡
የታመመ ድመት ካለ ንክኪን ማስወገድ ያስፈልጋል። በቤት ውስጥ ድመት እንኩዋን ባይኖር በአትክልት ስፍራ በመሳሰሉት አንዳንድ ስራን መስራት ካስፈለገ እጅን በጉዋንት መሸፈን ያስፈልጋል፡፡
ከድመት ጋር በተያያዘ ማንኛውንም ስራ ከሰሩ በሁዋላ እጅን እና የተጠቀሙበትን ጉዋንት ደህና አድርጎ መታጠብ ያስፈልጋል፡፡   
በግ፡-
የበግ ግልገሎች እና በጎች Toxoplasmosis የተባለው ጥገኛ ነብሳት አብሮአቸው ይኖራል፡፡ ይህም በሰው ልጅ ዘንድ የተለመደ አይነት ሲሆን Infection ያስከትላል፡፡ ይህ ሕመም እንደጉንፋን የመሳሰሉትን የሚያስከትል ሲሆን በተለይም ሴቶች በእርግዝና ወቅት ይህ ካጋጠማቸው ለሕጻኑ ጠንቅ ያስከትላል፡፡ በተለይም በእድሜ ወይንም በተለያየ ሕመም የአቅም መቀነስ ላለባቸው እንዲሁም ከኤችአይቪ ጋር በተያያዘ ሁኔታው ሲያጋጥም ከፍተኛ የሆነ የነርቭ ሕመም ሊያስ ከትል ይችላል፡፡ ስለዚህም የበግ ግልገሎችን በተቻለ መጠን መራቅ ወይም ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ሌላው ለInfection ከእናት ወደ ተረገዘው ልጅ መተላለፍ ምክንያት ከጉበት ጋር በተያያዘ የሚከሰተው ሔፒታይተስ በመባል የሚታወቀው ሕመም ነው፡፡
Hepatitis B
ሔፒታይተስ /ቢ/ አንዱ የቫይረስ አይነት ነው፡፡ ይህ ቫይረስ ጉበትን የሚያጠቃ ሲሆን ብዙ ጊዜ የህመም ምልክት ሳያሳይ ሊቆይና ካለባቸው ሰዎችም ወደሌላ ጥንቃቄ በጎደለው የወሲብ ግንኙነት እና ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር ቀጥታ ግንኙነት በማድረግ ነው፡፡ በእርግዝና ወቅት ቫይረሱ ያለባት ሴት በወሊድ ጊዜ ለጽንሱ እንደምታስተላልፈው እሙን ነው። ስለዚህም ማንኛዋም እርጉዝ ሴት በእርግዝና ወቅት ቫይረሱ በደምዋ ውስጥ መኖር ያለመኖሩ በምርመራ ስለሚረጋገጥ ለሚወለዱት ልጆች ገና እንደተወለዱ ክትባት እንዲወስዱ መደረግ አለበት፡፡ ልጆቹ ወደፊት ቫይረሱ እንዳይዛቸው ለማድረግ በተጨማሪም በ4/ 8/ 12/እና 16 ሳምንታቸው እንዲሁም የመጨረሻውን መድሀኒት በአንድ አመታቸው እንዲወስዱ መደረግ አለበት፡፡ በዚህም ከ90/እስከ 95% ልጆቹን ከከሄፒታይተስ ቢ ቫይረስ ነጻ ማድረግ ይቻላል፡፡
Hepatitis C
ሔፒታይተስ ሲ/የተባለው ቫይረስም  ልክ እንደ ሔፒታይተስ ቢ /ጉበትን የሚያጠቃ ነው፡፡ የሚለይበት መንገድ ግን በማንኛውም ቀጥታ ንክኪ የሚተላለፍ መሆኑ ነው፡፡ ደም የነካው መርፌ ፤ቫይረሱ ከያዘው ሰው ጋር ወሲብ በመፈጸም በመሳሰሉት ሁሉ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ እርጉዝ የሆነች ሴት ቫይረሱ ካለባት ለልጅዋ እንደምታስተላልፍ ታውቆ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ አደጋው እንደሔፒታይተስ ቢ ወይንም ኤችአይቪ አይደለም ቢባልም እንኩዋን መመረዙ ወደ ሌላ ሰው ወይንም ለልጅ መተተላለፉ የተረጋገጠ ነው፡፡ እንደ አለም አቀፉ የጤና ድርጅት (WHO) 2017/ መረጃ ሔፒታይተስ ሲ ክትባቱ ገና በምርምር ላይ ነው።

Read 1994 times