Sunday, 27 May 2018 00:00

ጣይቱ የባህል ማዕከል የኪነ-ጥበብ ምሽት ያካሂዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 መቀመጫውን በሰሜን አሜሪካ ያደረገውና በባህልና በኪነ ጥበብ ላይ አተኩሮ የሚሰራው  ጣይቱ የባህል ማዕከል፣ የፊታችን ረቡዕ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በአዲስ አበባ አክሱም ሆቴል የኪነ ጥበብ ምሽት ያካሂዳል፡፡ ገጣሚ ሰለሞን ሳህለና ደምሰው መርሻን ጨምሮ ወጣትና አንጋፋ ገጣሚያን የግጥም ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን የሃሳብ ቅብብሎሽ፣ ግለ ወግና ሌሎች ጥበባዊ ዝግጅቶች ይቀርባሉ ተብሏል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ “ፀሐዬ ደመቀች” በሚለው የህፃናት ህብረ ዝማሬ የሚታወቁት የአምባ ሙዚቀኞች፣ ከ25 ዓመታት በኋላ ተሰባስበው በመሳሪያ በተቀነባበረ ሙዚቃ ምሽቱን እንደሚያደምቁት የጣይቱ ባህልና የትምህርት ማዕከል፣ የአዲስ አበባ አስተባባሪ፣ ደራሲና ገጣሚ ይታገሱ ጌትነት ገልጿል፡፡

Read 2998 times