ሚዩዚክ ሜይዴይ ከኢትዮጵስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር፣ በጋዜጠኛ ዕዝራ እጅጉ በተሰናዳውና በፀሐፌ ትዕዛዝ ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተወልድ ሥራና ህይወት ዙሪያ በሚያጠነጥነው ቪሲዲ ላይ ነገ ከ8፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተ መፃህፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ ውይይት ያካሂዳል፡፡
ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርበው ራሱ ጋዜጠኛ ዕዝራ እጅጉ ሲሆን መድረኩ በቋንቋ መምህሩ ሰለሞን ተሰማ ጂ. እንደሚመራ ለማወቅ ተችሏል፡፡