Saturday, 26 May 2018 12:37

‹‹…መመረዝ (Infection) ከእናት ወደ ልጅ…››

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

አንዲት ሴት በሕይወት ዘመንዋ እንድታልፍበት ከሚፈለግ የህይወት ጉዞ አንዱ እርግዝናና በሰላም ልጅ ወልዶ መታቀፍ ነው፡፡ በእርግጥ የልጅ አባት መሆን ለአባቶችም እጅግ የሚያስ ደስት፤ በምንም ነገር ሊለወጥ ወይንም ሊገኝ የማይችል ተፈጥሮአዊ ሂደት ነው፡፡
አንዲት ሴት በእርግዝናዋ መደሰት እንደሚያጋጥማት ሁሉ የጤና መታወክ ሊገጥማት እንደ ሚችል ብዙ የምርምር ሂደቶች ያስረዳሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ክሪስቲን ኬሚ የተባሉ የህክምና ባለሙያ ማርች 29/2016 ለንባብ ያበቁት መረጃ አንዱ ነው፡፡ በዚህ መረጃ በእርግዝና ወቅት በሚከሰቱ የጤና እክሎች ምክንያት የሚደርሱት ጉዳቶች እና ምን የህክምና እርዳት እንደ ሚያስፈልገው እንዲሁም አስቀድሞ ለመከላከል ምን መደረግ እንዳለበት ተጠቅሶአል፡፡ ክሪስቲን ኬሚ እንደሚሉት በእርግዝና ወቅት በበሽታ መያዝን ወይንም መመረዝን (Infection) አስቀድሞ ማወቅ ወይንም መረዳት ጠቃሚ ነው፡፡  
እርግዝና አንዲት ሴት በሕይወት ዘመንዋ ሊያጋጥማት የሚችል ጤነኛና ትክክለኛው የህይወት ሂደት ነው፡፡ ነገር ግን እርግዝና በተለያዩ ምክንያቶች አንዲትን ሴት በሕመም ተጎጂ ሊያደርግ የሚችልበት ምክንያት ሊኖር እንደሚችል እና የሚገጥሙት ሕመሞችም በእርግዝና ላይ ላለች ሴት በቀላሉ ላይወገዱና ወደከፋ ደረጃ ሊደርሱ እንደሚችሉ አስቀድሞ መረዳት ያስፈልጋል፡፡  (Infection) ወይንም መመረዝ እናትየውን አስቀድሞውኑ ወደከፋ ደረጃ ሊያደርሱ የሚችሉ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በእንግዴ ልጅ አማካኝነት ወይንም ጽንሱ በሚወለድበት ጊዜ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ ይህ በሚያጋጥምበት ጊዜ የሚወለደው ጨቅላ ወደከፋ አደጋ ሊደርስ ይችላል፡፡  
በእርግዝና ጊዜ የሚፈጠሩ አንዳንድ መመረዞች (Infection) ጽንሱ ሳይወለድ በማህጸን እንዳለ እንዲሞት ሊያደርጉ ፤ካለጊዜው እንዲወለድ ወይንም ጽንሱ የተለያዩ የጤና እክሎች ማለትም የአካል መጉደል ወይንም ተሟልቶ ያለመፈጠር ችግሮችን ይዞ እንዲወለድ ወይንም በተከሰተው የአፈጣጠር ችግር ምክንያት ሕይወቱ እንዳይቀጥል የሚሆንበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል፡፡ የእናትየውም ሕይወት አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ በእርግዝና ወቅት የተከሰ ተውን ሕመም ለማስታገስ የሚወሰዱ መድሀኒቶች ለተፈጠረው ችግር አባባሽ የሆኑ የጎንዮሽ ጉዳቶች በተለይም ለሕጻኑ ሊፈጥርበት እንደሚችል አስቀድሞ መገመት ይገባል፡፡ ለማንኛውም በእርግዝና ወቅት ሊከሰት የሚችል መመረዝ (Infection) አስቀድሞ መከላከል ለእናትየውም ይሁን ለተጸነሰው ልጅ ጠቃሚ መሆኑ አይካድም ባለሙያዋ እንዳስነበቡት፡፡
በእርግዝና ላይ ያሉ ሴቶች ለሕመሞቹ ለምን ይጋለጣሉ ለሚለው መልሱ እርግዝናው በራሱ የሰውነትን ተፈጥሮአዊ ሁኔታ ስለሚያቃውሰው ነው፡፡ ሌላው ደግሞ በሰውነት ውስጥ ያለውን ሆርሞን መጠን ለውጥ እና የበሽታን የመቋቋም ኃይል ስለሚቀንስ በሽታን የመቋቋምን ኃይል ያዳክመዋል፡፡ የምጥና የወሊድ ወቅት በራሳቸው ጥንቃቄ ካልተደረገ በስተቀር ለእናትየውም ይሁን ለጨቅላው በበሽታ ለመያዝ የሚያስችሉበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡
በእርግዝና ጊዜ የበሽታ መቋቋም ኃይል (Immunity)፡-
Immunity - የሰውነት የበሽታ መቋቋም ኃይል መኖሩ ሰውነት በተቃራኒ ጎጂ ነገሮች በሚወ ረርበት ጊዜ እንዳይጠቃ የሚከላከል ነው፡፡ የሰውነት የመቋቋም ኃይል Immunity- ከባክቴሪያ እስከ ካንሰር ሴል ድረስ በመውለድም ይሁን በምጥ ወቅት እንዳይተላለፍ ማድረግ ይችላል፡፡ በእርግዝና ወቅት ተፈጥሮአዊው የበሽታ መከላከል ዘዴ እናትየውንም ሆነ ጽንሱን ከሚተላለፉ በሽታዎች ለመከላከል የራሱን ጥረት ያደርጋል፡፡ ይህም ምናልበናትም በእናትየው ላይ የደረሰው (Infection) ችግር ወደ ጽንሱ እንዳይተላለፍ ለማድረግ ያስችለዋል፡፡ ይህ ለውጥም  የተረገዘው ልጅ እንደውጭ አካል ተቆጥሮ በእናትየው መከላከያ ችግር እንዳይደርስበት ያግዛል፡፡ በአባባል የእናትየው ሰውነት የተረገዘውን ልጅ እንደባእድ አካል ወይንም እንደመጤ አለዚያም እንደ ሕመም ቆጥሮ ሊያስወግደው ይችላል ቢባልም በተግባር ግን የእናትና ልጅ ተፈጥሮአዊ ግን ኙነትን እንዲቋረጥ አያስችለውም ፡፡ በእርግጥ ልጅ ሲረገዝ በሰውነት ውስጥ የሚፈጠር እና ጊዜውን ጠብቆ የሚወጣ ማለትም ለዘለአለም የሰውነት አካል ሆኖ የማይቀጥል ነገር ግን ጽንስና እናት የው ግንኙነታቸው የግልም፤ ውጫዊም ሆኖ የእናትየው ሰውነት የመወለጃ ጊዜውን በትእግስት እንዲጠብቅ ተፈጥሮ ያስገድደዋል ፡፡ ስለዚ ህም የእናትየው በሽታን የመ ከላከል ዘዴ ልጁን አይጎዳውም፡፡  በእርግዝና ጊዜ የበሽታ መቋቋም ተፈጥሮአዊ ዘዴ ለአንድ ወይንም ለእናትየው ብቻ ሳይሆን ለልጁም ስለሆነ ከባድ ስራ ይጠብቀዋል፡፡
በእርዝግና ጊዜ የሰውነት ተፈጥሮአዊ ለውጥ፡-
የበሽታ መቋቋም ኃይልን ወደጎን አስቀምጠን በእርግዝና ወቅት ስለሚደርሰው የሰውነት ተፈጥሮአዊ ሁኔታዎች መዛባት ስንመለከት በሆርሞን መዛባት ምክንያት ከሚጎዱ የሰውነት ክፍሎች መካከል ከሽንት ጋር በተያያዘ የሚጠቀሱ ክፍሎች ዋነኞቹ ናቸው፡፡ እነርሱም፡-
Kidneys …(ኩላሊት)….ሽንትን የሚያመርት የሰውነት ክፍል፤
Ureters …ሽንትን ከኩላሊት ወደ ሽንት ፊኛ የሚያስተላልፈው ቱቦ ፤
Bladder …ሽንት የሚጠራቀምበት አካል፤
Urethra …. ሽንት ከሰውነት እንዲወጣ የሚጉዋጉዋዝበት ቱቦ፤
በእርግዝና ወቅት ማህጸን መጠኑ ስለሚሰፋና ክብደቱም ስለሚጨምር ከዚያው ጋር ተያይዞ ሰውነት ፕሮጀስትሮን የተባለውን ሆርሞን የማምረት መጠኑን ይጨምራል፡፡ የዚህ ሆርሞን መመረትም (Ureters) ሽንትን ከኩላሊት ወደ ፊኛ የሚያስተላልፈው ቱቦና (Bladder) ሽንት የሚጠራቀምበት አካል ጡንቻዎች እንዲላሉ ያደርጋል፡፡ ከዚህም የተነሳ ሽንት በሽንት ማጠራቀ ሚያ ውስጥ ቆይታውን ሊያራዝም ይችላል፡፡ የዚህ ውጤት ደግሞ የሽንት ቱቦ መመረዝን ሊያስከትል ይችላል፡፡
በእርግዝና ወቅት የሳንባ ፈሳሽ ከወትሮው በተለየ መጠኑን ይጨምራል፡፡ ሳንባ ፈሳሹ በመጨ መሩ ምክንያት በሳንባው በራሱና በሆድ እቃ ላይ ተጨማሪ ግፊት ያደርጋል፡፡ ይህም ሰውነት ፈሳሹን ለማስወገድ እንዲቸገር ያደርገዋል፡፡ በሳንባ ሊኖር ከሚገባው በላይ የተጨመ ረው ፈሳሽም የባክቴሪያ እድገትን ከማፋጠኑም በላይ ሰውነት የተከሰተውን ኢንፌክሽን ለመቋ ቋም እንዳይችል ያደርገዋል፡፡ ባጠቃላይም በእርግዝና ወቅት በሳንባ ላይ የሚጨመረው ፈሳሽ Pneumonis  የተሰኘውን ኢንፌክስን እንዲፈጠር ያደርገዋል፡፡  
ከላይ በእርግዝና ጊዜ ይከሰታሉ ተብለው የተጠቀሱትን የተለያዩ ምክንያቶች ተከትሎ በእና ትየውም ይሁን በጽንሱ ላይ የሚደርሱ አደጋዎች ካልተከላከሉዋቸው እስከ ሕልፈት ሊያደርሱ እንደሚችሉ ባለሙያዎቹ ይገልጻሉ፡፡
በእናትየው ላይ የሚደርስ ችግር፡-
በእርግዝና ወቅት ከሚከሰቱት ኢንፌክሽኖች መካከል አንዳንዶቹ ችግሩን በእናትየው እንዲያበቃ ያደርጋሉ፡፡ ሕመሞቹም በሽንት ቧንቧ እና አካበቢዎች በብልት እና ከወሊድ በሁዋላም ሊኖር የሚችል ነው፡፡
በልጁ ላይ የሚደርስ ችግር፡-
በእርግዝና ወቅት ከሚከሰቱት ኢንፌክሽኖች መካከል በተለይም በሕክምናው አጠራር cytomegalovirus, toxoplasmosis እና parvovirus ከተባሉት ቫይረሶች የሚከሰተው ኢንፌክሽን በቀጥታ ከእናት ወደ ልጅ መተላለፍ የሚችሉ ናቸው ፡፡ ይህም ውጤቱ እጅግ አስከፊ ነው ፡፡ ከተጠቀሱት ውስጥ በመውለድ ጊዜ ለሚከሰተው cytomegalovirus ለተባለው ቫይረስ የሚደረገው የህክምና እርዳታ እጅግም አመርቂ አይ ደለም፡፡ toxoplasmosis ለተባለው ግን መመረዝን ለመከላከል የሚደረግ የህክምና ዘዴ ሲኖር ለ parvovirus ግን መከላከል እንኩዋን ባይቻል ኢንፌክሽኑ ከተከሰተ በሁዋላ ግን ደምን በመተካት ሕክምና ሕጻኑ ሊረዳ ይችላል፡፡ እንደባለሙያዎቹ እማኝነት፡፡   
በእርግዝና ላይ ያሉ ሴቶች በአኑዋኑዋራቸው ወይንም ከሚያሳድጉዋቸው የቤት እንስሳት ጋር በተያያዘ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ኢንፌክሽን ወይንም መመረዝ ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡
ይቀጥላል

Read 2491 times