Monday, 21 May 2018 00:00

“ዝክረ ኪነ ጥበብ ፌስቲቫል” ከትናንት በስቲያ ተጠናቀቀ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከኢትዮጵያ የባህል ማዕከልና ከሙሉዓለም አዳራሽ ጋር በመተባበር፣ በባህር ዳር ከተማ ሙሉዓለም አዳራሽ “ዝክረ ኪነ ጥበብ ፌስቲቫል” በሚል ለአምስት ተከታታይ ቀናት ተካሄደ፡፡
“ኪነ ጥበብ ለሰላማችንና ለሀገራዊ አንድነታችን” በሚል መሪ ቃል ለ13ኛ ጊዜ በተካሄደው በዚህ ፌስቲቫል፤ የክልሉ የባህልና ቴአትር ስራዎች፣ ክልሉን የሚወክሉ የሙዚቃና የባህል ዝግጅቶች፣ የፋሽን ትርኢቶች፣ የግጥምና የሥነ ፅሑፍ ስራዎች የቀረቡ ሲሆን የዕደ ጥበብ ምርቶች አውደ ርዕይም ለዕይታ ቀርቦ ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በኪነ ጥበቡ ዘርፍ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸውና ጉልህ አስተዋፅኦ ሲያበረክቱ የቆዩ አንጋፋ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና በዘርፉ የበኩላቸውን እየተወጡ የሚገኙ ወጣት ከያንያን እንደተዘከሩና እንደተሸለሙም የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡

Read 2162 times