Monday, 21 May 2018 00:00

ሁለተኛው “ጣና ሽልማት” ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ባለፈው ዓመት በባህርዳር ከተማ በማህበራዊ ሚዲያ ጉልህ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ድርጅቶችንና ግለሰቦችን የሸለመው “ጣና ሽልማት” ሁለተኛው ዙር ጳጉሜ 1 ቀን 2010 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ ይካሄዳል ባለፈው ዓመት በ10 ዘርፍ ሽልማቶችን የሰጠው ድርጅቱ ዘንድሮ ወደ 16 ዘርፎች ማሳደጉን ገልፆ ተወዳዳሪዎችን ከወዲሁ መመዝገብ እንደጀመረ አዘጋጆቹ “ሰለሞኒክ ኢንተርቴይመንትና” ዘመራ መልቲ ሚዲያ ሀላፊዎች ተናግረዋል፡፡
ሽልማት ከሚሰጥባቸው ዘርፎች መካከል በፈጣን ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃ፣ በባህልና ቱሪዝም፣ በታሪክ በስፖት መረጃ፣ በጤና፣ በስነ ፅሑፍ፣ በንግድና ቢዝነስ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ በስነ-ጥበባዊ ምስሎችና ትርክቶች፣ በፎቶግራፍ በትምህርትና በማህበረሰብ ግልጋሎት፣ በጥናትና ምርምር ዘርፍ እና በበጎ አድራጎትና በአካባቢ ልማት ዘርፎች ተጠቃሾች ናቸው፡፡

Read 2483 times