Monday, 07 May 2018 08:52

ሱዳንና ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድቡን በጋራ ለመጠበቅ ተስማሙ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(3 votes)

  “ዘገባው ከእውነት የራቀ ነው” - የውጭ ጉ/ሚ

    ኢትዮጵያና ሱዳን በጋራ ወታደራዊ ኃይል ገንዘብ 64 በመቶ የደረሰውን ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለመጠበቅ መስማማታቸውን “ሚድል ኢስት ሞኒተር” የዘገበ ሲሆን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፤ ዘገባው ሃሰተኛ ነው ብሏል፡፡
የሱዳን ጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ከማል አብዱል ማሩፍ አልማሂ እና የኢትዮጵያ አቻቸው ጀነራል ሳሞራ የኑስ ሰሞኑን ተገናኝተው በጋራ ወታደራዊ ፕሮቶኮል ላይ መወያየታቸውን የጠቆመው ዘገባው፤ የሁለቱን ሀገራትን ድንበር በጋራ ለመጠበቅና የህዳሴውን ግድብም ከማንኛውም ጥቃት በጋራ ለመከላከል ተስማምተዋል ብሏል፡፡
ሁለቱ የጦር አዛዦች ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርንና የመሳሪያ እንዲሁም የአደንዛዥ እፅ ዝውውርን በጋራ ለመቆጣጠርም ተስማምተዋል ሲል - ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም በበኩላቸው፤ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ኢትዮጵያውያን እንደ አይን ብሌናቸው የሚመለከቱት የሉአላዊነታቸው መገለጫ ነው፤ የሚጠበቀውም በኢትዮጵያ ህዝብ ነው የሱዳንና የኢትዮጵያ መንግስታት ፈፅሞ እንደዚህ አይነት ስምምነት ሊፈፅሙ ቀርቶ ጨርሶ አልታሰበም” በማለት ዘገባው ከእውነት የራቀ፣ ነጭ ውሸት ነው” ብለዋል - አቶ መለስ

Read 5394 times