Sunday, 29 April 2018 00:00

በ3 ወራት ፌስቡክ 11.9 ቢ. ዶላር ገቢ፤ ሳምሰንግ 10.8 ቢ. ዶላር ትርፍ አግኘተዋል

Written by 
Rate this item
(2 votes)

 የታዋቂው ማህበራዊ ድረገጽ ፌስቡክ የመጀመሪያው ሩብ አመት አጠቃላይ ገቢ ካለፈው አመት ተመሳሳይ ጊዜ በግማሽ ያህል መጨመሩን የዘገበው አልጀዚራ፤ ፌስቡክ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ 11.96 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ገልጧል።
ተቀማጭነቱን በካሊፎርኒያ ያደረገው ፌስቡክ ምንም እንኳን በመረጃ ቅሌት ቀውስ ውስጥ ቢሆንም ገቢውና የተጠቃሚዎቹ ቁጥር መጨመሩንና የተጠቃሚዎቹ ቁጥር ባለፉት ሶስት ወራት በ13 በመቶ በማደግ፣ 2.2 ቢሊዮን መድረሱን ባለፈው ረቡዕ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
በተመሳሳይ ዜናም የደቡብ ኮርያው ሳምሰንግ ኤሌክትሮኒክስ ለተከታታይ አራት ሩብ አመታት ክብረወሰን ያስመዘገበበትን ትርፍ ማግኘቱ የተዘገበ ሲሆን ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ 10.8 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ እንዳገኘ ተነግሯል፡፡
ሳምሰንግ በሚሞሪ ቺፕስና በጋላክሲ ኤስ 9 ስማርት ፎን ምርቶቹ ላይ ያለው የገበያ ፍላጎት ማደጉ ከፍተኛውን ትርፍ እንዲያገኝ አስችሎታል መባሉን የዘገበው ቴክ ግሎባል፤ 73 በመቶ የሚሆነውን ትርፍ ያገኘው ከሚሞሪ ቺፕስ ሽያጭ መሆኑንም አመልክቷል፡፡

Read 1490 times