Saturday, 21 April 2018 11:42

“ህይወት ምርጫ ነው” መፅሐፍ ነገ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 ከግብርና ከምግብ ዋስትናና ከዕፅዋት ጋር የተያያዙ ትምህርቶች ያጠኑትና በደቡብ ክልል በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ያገለገሉት ዶ/ር በላይ ደርዛ “ህይወት ምርጫ ነው” የተሰኘ መፅሐፍ ነገ ከረፋዱ 4፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተ - መፃሕፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ ይመረቃል፡፡ በዕለቱ አንጋፋዎች ደራሲያን ፀሐይ መላኩ፣ የዝና ወርቁ፣ ጋዜጠኞቹ እሸቱ ገለቱ እና ቅጣው ንጉሴ፣ አርቲስት ዋሲሆን በላይና ወጣት ገጣሚያን ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡
መፅሐፉ በዋናነት የሚኖረው ህይወት በራሱ በግለሰቡ ምርጫ ላይ የሚወሰን እንደሆነ የሚገልፅ ነው፡፡ ለዚህም “… ህይወታችን የምርጫችን ውጤት ምርጫችን ማንነታችንን ይወስናል፡፡ ሁሌም ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነቃ ሁለት ምርጫዎች አሉህ ከራዕይህ ጋር መኝታህን መቀጠል ወይም ተነስተህ ራዕይህን ለማሳካት መስራት …” ይላል በመፅሃፉ ጀርባ የተቀመጠው ማስታወሻ በ164 ገፅ የተቀነበበው መፅሐፉ በ80 ብር እና በ20 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 2222 times