Sunday, 01 April 2018 00:00

የስነተዋልዶ ጤና መብቶች

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

 የስነተዋልዶ ጤና መበቶች በሰብዐዊ መብቶች ላይ የተመሰረቱ እና ለጾታ እና ለስነተዋልዶ የሚያገለግሉ መብቶች ናቸው፡፡ እነዚህ መብቶች በአራት የተለያዩ ክፍሎች የተጣመሪ ሲሆን፤ ለስነተዋልዶ ጤና መብቶች ስንጠቀምባቸው አንዳቸው ካንዳቸው ጋር ያላቸው ተዛዶ እጅጉን የጠበቀ ነው፡፡ እነሱ፤
የስነጾታ ጤና፤
የስነጾታ መብት
የስነተዋልዶ ጤና እና
የስነተዋልዶ መብት ናቸው። በስነጾታ፤ እና በስነተዋልዶ ጤና እና መብት ጥናት ውስጥ እነዚህን አራት ሃሳቦች ለያይተን የምንጠቀምባቸው ሲሆን አንዳቸው ከሌላኛው ጋር ያለው ዝምድና ግን እጅጉ ከፍተኛ ነው፡፡
የስነጾታ እና የስነተዋልዶ ጤና በአብዛኛው አንዱ ሌላኛውን እንደሚተኩ አድርገን የምንጠቀምባቸው አገላለጾ ሲሆኑ፤ የስነጾታ እና የስነተዋልዶ መብቶችንም እንዲሁ አንዱ ሌላውን የሚተካ ሃሳብ ተደርጎ መጠቀሙ የተለመደ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የስነተጾታ መብት በስነጾታ ጤና ውስጥ ተካቶ፤ አሊያ ግልባጩን ማግኘት የተለመደ ነው፡፡ የተለያዩ የቃላት አጠቃቀሞች በተለያዩ መንግስታዊ ባሆኑ ድርጅቶች መኖቸው ብቻ ሳይሆን፤ በአንድ መንግስታዊ ባሆነ ድርጅት ውስጥም የተለያየ የቃላት አጠቃቀም ይስተዋላል፡፡
በጉዳዩ ላይ ከሚሰሩ አለም አቀፍ የተረዐዶ ድርጅቶች መካከል የአለምአቀፍ የታቀደ ወላጅነት ፌደሬሽን፤ የአለምአቀፍ የስነጾታ ማህበር፤ እንዲሁም የአለም አቀፍ የኤች አይ ቪ አድስ ትብብር ይገኙበታል፡፡
የአለምአቀፌ የጤና ድርጅት የስነጾታ ጤናን እንዲህ ይተረጉመዋል- የስነጾታ ጤና ማለት ከጾታ ጋር በተገናኘ የአካላዊ የስነልቦናዊ እንዲሁም የማህበራዊ ደህንነትን ያመለክታል፡፡ ይህም በመልምነት እና በመከባበር ላይ የተሞላ አመለካከት ለስነጾታ፤ ለጾታዊ ግንኙነቶች እና በማናቸውም ሃይል የተሞላበት ድርጊት ላይ ያልተመረኮዘ የስነጾታ ግንኙነትን መፈለግ ያንንም ለመከነወን መቻልን ያመለክታል፡፡
ከሌሎች ከሶስቱ ጽንሰ ሃሳቦች በተለየ መልኩ የስነጾታ መብት በጾታዊ ግንኙነት መደሰት መቻልን እና ስሜትን በነጻነት መግለጽ መቻል ላይ ያተኩራል፡፡ ይህን መብት ለመታገል የሚደረገው ትግል ከሚደረግባቸው ተጨባጭ መሰረቶች አንዱ የአለምአቀፉ የስነጾታ መብት ማህበር የደነገገው ድንጋጌ ነው፡፡ በ14ኛው በአለምአቀፉ የስነጾታ ኮንግረስ ወቅት ማለትም በሆንግ ኮንግ እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1999 አ/ም በተካሄደው፤ ማህበሩ 14 ነጥቦች ያሉት የስነጾታ መብቶችን አውጥቶ አጸድቆ ነበር፡፡ በኋላ ላይ በመጋቢት 2014 ደግሞ ተጨማሪ 14 ነጥቦች አካቶ ስራ ላይ ውሏል። በስተመጨረሻ በጸደረገ ክለሳ አሁን የምንጠቀምባቸው 16 የስነጾታ መብቶች ላይ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
የእኩልት እና ከአድሎ ነጻ የመሆን መብት፤
የራስን መብት በራስ የመወሰን መብት
የህይወት፤ የነጻነት እንዲሁም የደህንነት መብት፤
ከሰብዐዊ ካልሆኑ ቅጣቶች ነጻ የመሆን መብት፤
ከማቸውም ጥቃትና አስገዳጅ ሁኔታዎች ነጻ የመሆን መብት፤
 የግለኝነት መብት
ሁኔታዊ የሚፈውደውን የተሻለ የጤና፤ የስነጾታ ጤና አገልግሎትን ጨምሮ የማግኘት፤ ድህንነቱ የተጠበቀ የስነጻታ እርካታን የማግኘት መብት
የሳይንሳዊ ግኝቶችን እና እነሱን ተከትሎ የሚመጡ የጤና አገልግሎት ውጤቶችና ጥቅሞቻቸውን የማግኘት መብት፤
መረጃን የማግኘት መብት
 ለትምህርት እና ለሁሉን አቀፍ የስነጾታ ትምህርት የማግኘት መብት
ትዳርን እና መሰል ግንኙነቶችን የመመስረት፤ ወይም በትክክለኛ መረጃ እና በእኩልነት ላይ በተሰረት መልኩ የማፍረስ መብት
ልጆችን ለማፍራት፤ የሚያፈሩበትን ጊዜ እና ቁጥሩን የመወሰን እና ያንንም ለማድረግ የሚያስችል መረጃን የማግኘት መብት፤
ሃሳብን በነጻነት የማንጸባቅ መብት፤
በማበር የመደራጀት እንዲሁም ሰላማዊ ስብሰባዎችን የማድረግ መብት
በፖለቲካና በማበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ የመሳተፍ መብት
ፍትህን፤ እና ይግባኝን የማግኘት መብት
የሚሉት ናቸው፡፡ እነዚህም ድንጋጌውች ቆይተው የዮጋካርታ ድንጋጌ ተብ ለሚጠራው እና በመጋቢት 2007 ለወጣው ድንጋጌ መሰረት ጥለዋል፡፡

Read 1920 times