Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 28 April 2012 14:13

ጃኖ ባንድ በአለማቀፍ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ላይ አነጣጥሯል

Written by 
Rate this item
(2 votes)

ባለፈው ማክሰኞ በሸራተን አዲስ ጋዝ ላይት ባቀረበው የሙዚቃ ዝግጅት ነው ጃኖ ባንድ ስራውን“ሀ” ብሎ የጀመረው። አስር ወጣት ኢትዮጵያውያን ሙዚቀኞችንና ድምፃዊያንን ያካተተው ጃኖ ባንድ፤ ከእስካሁኖቹ የአገራችን የሙዚቃ ቡድኖች ለየት የሚለው፤ የሮክ ባንድ በመሆኑ ብቻ አይደለም። ገና ከጅምሩ፤ የአሜሪካና የአውሮፓ መድረኮችን በማነጣጠር የተቋቋመ መሆኑም ልዩ ያደርገዋል። ካሁን በፊት በውጭው አለም ስኬታማ የሆኑ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቡድኖች አልነበሩም ማለት አይደለም። አዲስ ገሰሰን ጨምሮ ኢትዮጵያዊያን ሙዚቀኞችን ያካተተው ዳሎል ባንድ በአሜሪካ ስኬታማ እንደነበረ ይታወቃል።ሁለትአመትበተከታታይየግራሚሽልማትያገኙኢትዮጵያዊያንሙዚቀኞች፤ የዳሎል ባንድ አባላት የነበሩ ናቸው። የዳሎል ባንድና የሙዚቀኞቹ ስኬት በአብዛኛው በሬጌ ሙዚቃ ዙሪያ ነበር። ያኔ በአሜሪካ የሙዚቃ ኢንዱስትሪና የሙዚቃ አፍቃሪ ዘንድ የሬጌ ሙዚቃ እንደ ፋሽን የሚታይ ነበር የሚለው ሙዚቀኛና ድምፃዊ ሄኖክ መሃሪ፤ የአፍሪካ የሙዚቃ ጣእም በአሜሪካ ውስጥ ገና ብርቅ በነበረበት በዚያ ወቅት የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች አዲስ ለውጥ ለመፍጠር ጥረዋል፤ በስኬትም ታሪክ ሰርተዋል ብሏል።

የኛ ትውልድም ባለፉት አመታት አዲስ ነገር ለመፍጠር እንደሰራነው ሁሉ አሁን ደግሞ ታሪክ ለመፍጠር የሚጥሩ ወጣቶች ያሉበት ጃኖ ባንድ መቋቋሙ ያስደስታል ብሏል። በእርግጥ፤ በእድሜ የሚለያዩት የሙዚቃ ትውልዶች አዲስ ለውጥ ለመፍጠር የሚጥሩት፤ የግድ ለየብቻ በመነጣጠል አይደለም። በወጣቶች የተዋቀረውን ጃኖ ባንድ በመሪነት ካቋቋሙት ሶስት ሰዎች መካከል አንዱ የሆነው አዲስ ገሰሰ፤ የዳሎል ባንድ አባል የነበረና በአሜሪካ ለበርካታ አመታት በሙዚቃው ኢንዱስትሪ ሲሰራ የቆየ የሙዚቃው አለም ቤተኛው።አዲስገሰሰ፤ወደኢትዮጵያ ከተመለሰ ወዲህ ለበርካታ አመታት ሲመኘውና ሲያስበው የነበረ ጉዳይ ቢኖር፤ ወጣቶችን ያሰባሰበ የሙዚቃ ባንድ ማቋቋም ነው - በአለማቀፍ የሙዚቃ መድረክና ኢንዱስትሪ የሚሳተፍ የወጣቶች ባንድ። እንደተመኘውም እየሆነለት ነው። በአሜሪካ በርካታ የሙዚቃ አልበሞችን ፕሮዲዩስ በማድረግ ስም ያተረው የጂጂ ባለቤት ቢል ላውዌል ሌላኛው የጃኖ ባንድ ፕሮዱዩሰር ነው። ሌላኛውስ? በአሜሪካ፣ በኒውዮርክ የቢዝነስእምብርት ውስጥ በኢንቨስትመንት ስራዎች ላይ ልምድ ቀስሞ፤ ከዚያም በኢትዮጵያ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ሃሳቦችን ወደ ተግባር በመቀየርና ስኬት በማስመዝገብ ክብር የተጎናፀፈው የቢዝነስ አዋቂ ኤርሚያስ አመልጋ ነው። የሶስቱ ሰዎች ውጤት ነው - ጃኖ ባንድ። ግን ደግሞ፤ የአስር ወጣት ሙዚቀኞች የወደፊት ህይወት ነው - ጃኖ ባንድ።ጃኖ ባንድ፤ አገርኛ ዜማዎችና ቅኝቶችን በሮክ ስልት ለአድማጭና ለተመልካች በማቅረብ ስራውን የጀመረው ባለፈው ማክሰኞ እለት ቢሆንም፤ ባለፉት አስር ወራትም ይህንኑን ሲሰራ ነው የቆየው። የባንዱ ወጣት አባላት፤ የሙዚቃ መሳሪያና የመለማመጃ ቦታ ተሟልቶላቸው፤ የመጀመሪያ ስራቸውን ከማቅረባቸው በፊት ለወራት ያለማቋረጥ ሲለማመዱና ሲያጠኑ ከርመዋል። የባንዱ አመንጪዎችና ፕሮዲዩሰሮች፤ ኤርሚያስ አመልጋ፣ አዲስ ገሰሰና ቢል ላስዌል  ...እዚህ ላይ ብልህነታቸውን ብቻ ሳይሆን ከምር ሃሳባቸውን እውን ለማድረግ የቆረጡ መሆናቸውን አሳይተዋል። አስር የልምምድና የጥናት ወራቶችን ማሳለፍ ቀላል አይደለም - ወጪንና ትእግስትን ይጠይቃል። ነገር ግን፤ ባለፈው ማክሰኞ እንደታየው፤ ውጤቱ ያረካል። የአዲስ ገሰሰ እርካታ ሁለት መልክ አለው። ከአድማጭና ከተመልካች ያገኘነው ምላሽ በጣም ያረካል ያለው አዲስ ገሰሰ፤ ከጠበቅነው በላይ በጣም አስደሳች ምላሽማግኘታችን ለወደፊት ብርታት ይሆነናል ብሏል። በሙዚቃ አዋቂነቱም፤ የጃኖ ባንድ የሙዚቃ ድግስ፤ በጣም ድንቅ ነው ብሏል - አዲስ ገሰሰ። ኢትዮጵያን ሙዚቃ በአለማቀፍ የጥራት ደረጃ ለማሳደግ ነው የምንፈልገው የሚለው አዲስ ገሰሰ፤ የማክሰኞው የሙዚቃ ዝግጅት በጣም ጥሩ ነበርየምለውም በዚሁ መንገድ ነው ብሏል። ሄኖክ መሃሪ በበኩሉ፤ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቾቹ ከጠበቅኩት በላይ አርክተውኛል፤ አንድምእንከንላወጣላቸው አልችልም በማለት አድናቆቱን ገልጿል። አብዛኞቹን ሙዚቀኞችና ሁለቱን ድምፃዊያን ካሁን በፊትም በሙዚቃ ስራ እንደሚያውቃቸው ሄኖክ ጠቅሶ፤ በሮክ ስልት የዲባ አዘፋፈን አሳማኝ ነው ብሏል። ለሙዚቃ ዝግጅት የሚደረግ ልምምድ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ከማክሰኞው ትእይንት መረዳት እንደሚቻል የገለፀ ሙዚቀኛ፤ የባንዱ አባላት የመድረክ እንቅስቃሴ በደንብ የተጠና ነው ብሏል።የጃኖ ባንድ፤ በቅርቡ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች በ10 ዩኒቨሪሲቲዎች የሙዚቃ ዝግጅት እንደሚያቀርብ የገለፀው አዲስ ገሰሰ፤ ከዚያ ቀጥለንም በአሜሪካ እና በአውሮፓ የሙዚቃ ዝግጅቶችን ለማቅርብ ፕሮግራም እያወጣን ነው ብሏል። በአሜሪካ ዳሎል ባንድንና የቦብ ማርሊ ቤተሰቦችን በመያዝ በየከተማውና በየዩኒቨሪሲቲው የሙዚቃ ዝግጅት ስናቀርብ ስኬታማ ነበርን በማለት ያስታወሰው አዲስ ገሰሰ፤ አሁንም የጃኖ ባንድ ስኬታማ እንደሚሆን አልጠራጠርም ብሏል። ባንዱ ስኬታማ ሊሆን እንደሚችል የሚያምነው ሄኖክ መሃሪ፤ አሁን የሮክ ሙዚቃ በአሜሪካ ፋሽን እየሆነ መምጣቱ ለባንዱ ስኬት ጥሩ ነው ብሏል። በእርግጥ፤ እነ ዳሎል ከነበሩበት ጊዜ ይልቅ፤ አሁን የሙዚቃ ኢንዱስትሪው በበርካታ ምርጫዎች የተጣበበና ብርቱ ፉክክር ያለበት ነው የሚለው ሄኖክ፤ የጃኖ ባንድ ውጤት ምን እንደሚሆን ወደፊት የምናየው ይሆናል፤ ነገር ግን አዲስ ለውጥ ለመፍጠር ታስቦ ጃኖ ባንድ መቋቋሙ ራሱ በጣም አስደሳች ነው ብሏል።

 

 

 

 

Read 24010 times Last modified on Saturday, 28 April 2012 14:21