Saturday, 28 April 2012 13:27

የኮርያ ዘማቾች በሙዚቃ ዝግጅት ይታሰባሉ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

ከ61 ዓመት በፊት ወደ ኮርያ ዘምተው ህይወታቸው ያለፈ ኢትዮጵያውያን ዛሬ በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስትያን እና በኮርያ ዘማቾች ፓርክ በሚደረጉ የተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚታሰቡ ተገለፀ፡፡ በኮርያ ዘመቻ የሞቱ 122 ኢትዮጵያውያን ወታደሮች አጽም ተሰብስቦ ባረፈበት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክርስትያን ፀሎት የሚደረግ ሲሆን ስድስት ኪሎ አፍንጮ በር አካባቢ በሚገኘው የኮርያ ዘማቾች መታሰቢያ ፓርክም በሙዚቃ ዝግጅት እንደሚከበር የኢትዮጵያ - ኮርያ ዘማቾች ማህበር አስታወቀ፡፡ ከ20 ዓመት በፊት የተመሠረተው ማህበር በዓለም ዙሪያ ካሉ አቻ ማህበራት አንዱ ሲሆን ለምስረታው የደቡብ ኮርያ መንግስትና ሕዝብ እንዲሁም የአዲስ አበባ አስተዳደር ከፍተኛ እገዛ አድርገውለታል፡፡

የማህበሩ ፕሬዚዳንት ኮሎኔል መለስ ተሰማ፤ “ይህን ታሪክ ለማስተላለፍ ሃላፊዎቹ የወጣቱ ትውልድ ጋዜጠኞች ናችሁ፡፡” ብለዋል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በቹንቾን ከሰፈሩት የያኔው የቃኘው ሻለቃ አባላት ውስጥ አንዳቸውም ያልተማረኩ ሲሆን በሕይወት ያሉት አባላት አሁን ዕድሜያቸው ከ80 ዓመት በላይ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ቃኘው የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አባት የራስ መኮንን የፈረስ ስም ነበር፡፡

 

 

Read 956 times Last modified on Saturday, 28 April 2012 13:29