Saturday, 07 April 2018 00:00

ኩዌት በኢትዮጵያ የቤት ሠራተኞች ላይ የጣለችውን እገዳ አነሳች

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(5 votes)

 ኩዌት ወደ ሃገሬ እንዳይገቡ ስትል በኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞች ላይ ለአመታት ጥላው የነበረውን እገዳ ማንሣቷ አስታወቀች። የኩዌት የዜና አገልግሎት ባሠራጨው ዘገባ፤ በኢትዮጵያና በኩዌት መንግስታት መካከል በተደረሰ ስምምነት መሰረት እገዳው ተነስቷል ብሏል፡፡
የኩዌት የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሜጀር ጀነራል ሼኪ ማዜን አል-ሣባ ከኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች ጋር ባደረጉት ድርድር፤ ከረቡዕ መጋቢት 26 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ የቤት ሠራተኞች ወደ ኩዌት  እንዲገቡ ተፈቅዷል፡፡
የኩዌት መንግስት ወደ ሃገሩ የሚገቡ ኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞች ደህንነታቸው የሚጠበቅበትን ሁኔታ በተመለከተ  መፈረሙም ታውቋል፡፡ ኩዌት ኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞች ወደ ሃገሯ እንዳይገቡ አግዳ  የነበረው አደንዛዥ እፆችን ሲያዘዋውሩ ደርሼበታለሁ በሚል እንደነበር ታውቋል፡፡

Read 3268 times