Tuesday, 20 March 2018 11:16

“ምሳሌያዊ አነጋገር” ለገበያ ቀረበ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(4 votes)


    በመምህርት፣ ደራሲና ጋዜጠኛ ወይንሸት በየነ የተዘጋጀ “ምሳሌያዊ አነጋገር፣ ሥነ-ፍቺያዊ ፋይዳና አንድምታ” የተሰኘ መፅሐፍ በገበያ ላይ ዋለ፡፡
መፅሐፉ በ3 ምዕራፎች የተከፈለ ሲሆን የመጀመሪያው ምዕራፍ የምሳሌያዊ አነጋገር ሥነፍቻዊ ፋይዳና አንድምታን የያዘ ነው፤ በሁለተኛው ምዕራፍ የምሳሌያዊ አነጋገር ፍቺዎችን የሚያሳይ ሲሆን የመጨረሻው ምዕራፍ ደግሞ አቻ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን የያዘ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
የቋንቋ፤ የስነ መለኮት፣ የማህበረሰብ ሳይንስ፣ የፍልስፍናና የልጆች ሁለንተናዊ ዕድገት  ተመራማሪ ዮናስ ዘውዴ ከበደ በመፅሐፉ የጀርባ ሽፋን ላይ ባሰፈሩት አስተያየት፤ “ይህ መጽሐፍ ለቋንቋ ተማሪዎች፣ አስተማሪዎችና ተመራማሪዎች ራሱን የቻለ በጎ አስተዋፅኦ ያደርጋል ብዬ አስባለሁ። ይዞ የተነሳቸው አንኳር ርዕሰ ጉዳዮች በተለይ ለአማርኛ ሥነ ፅሁፍ፣ ሥነ ቃልና ተረትና ምሳሌ ላይ ዕውቀታችንን ለማዳበር የበኩሉን አስተዋፅኦ ያበረክታል ብዬ አምናለሁ…” ብለዋል፡፡
በ261 ገፆች የተዘጋጀው መፅሐፉ፤ በ91 ብር ከ25 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡ ወይንሸት ከዚህ ቀደም “ተቀባይ የሌለው መልዕክትና ሌሎች አጫጭር ልቦለዶች” እና ለ9ኛና 10ኛ ክፍል የርቀት ተማሪዎች የቋንቋ መማሪያ ማዘጋጀቷ ታውቋል፡፡

Read 6220 times