Sunday, 04 March 2018 00:00

“ዝክረ አድዋ” የስዕል ኤግዚቢሽን ሐሙስ ተከፈተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(9 votes)

ዘንድሮ ለ122ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ የተሰሩ ሥዕሎች የሚታዩበት “ዝክረ አድዋ” የተሰኘ የስዕል አውደ ርዕይ ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በጣይቱ ሆቴል መታየት ጀምሯል፡፡
ከ15 ሰዓሊያን በላይ ስራቸውን ለእይታ ያቀረቡበት ይህ አውደ ርዕይ፤ የአድዋን ጦርነትና ድል አጠቃላይ ታሪክ የሚያሳዩ ስራዎች ለእይታ የቀረቡበት እንደሆነና ለአንድ ሳምንት ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ታውቋል፡፡  ሰዓሊያኑ ባለፈው አመትም በተመሳሳይ አድዋን ለመዘከር የተሰሩ ስራዎቻቸውን ለእይታ ማብቃታቸውንና በተቻለ መጠን በየዓመቱ “ዝክረ አድዋ”” የስዕል አውደ ርዕይ በማሳየት እንደሚቀጥሉ ተገልጿል፡፡

Read 9884 times