Saturday, 24 February 2018 12:50

21ኛዋ የዓለም ዋንጫ ዛሬና ነገ በኢትዮጵያ ናት

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(2 votes)

 21ኛዋ የዓለም ዋንጫ ዛሬና ነገ ኢትዮጵያ ውስጥ ናት፡፡ በዛሬው ዕለት በልዩ የኮካ ኮላ ቻርተር አውሮፕላን ከሱዳን ካርቱም በመነሳት ረፋዱ ላይ አዲስ አበባ የምትገባ የዓለም ዋንጫዋን የመንግስት ሃላፊዎች፤ የእግር ኳስ ፌደሬሽን ሃላፊዎችና ሰራተኞች፤ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ተወካይ እንዲሁም የሚዲያ ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለሙያዎች አቀባበል ያደርጉላታል፡፡ ዋንጫውን ይዞ ከሚመጣ የፊፋ ቡድን ጋር በኢትዮጵያ ሀ 17 ሁለቱም ፆታ ብሄራዊ ቡድኖች የተመረጡ ሁለት የኮፓ ኮካ ኮላ ውድድር ታዳጊዎች ይኖራሉ፡፡ ከአየር መንገድ በመነሳት የዓለም ዋንጫዋ በቀጥታ ወደ ብሄራዊ ቤተመንግስት በማቅናት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት የእንኳን ደህና መጣሽ አቀባበል ይደረግላታል፡፡ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስተር ተወካይ እንዲሁም የእግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት የእንኳን ደህና መጣሽ ንግግር ካሰሙ በኋላ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳት ዶክተር ሙላቱ ተሾመን ለንግግር ይጋብዛሉ ፡፡ ፕሬዝዳንቱ ንግግር አሰምተው ዋንጫዋን በብሄራዊ ቤተመንግስት ያነሷታል፡፡ በነገው ዕለት ደግሞ በሂልተን ሆቴል ለእይታ ስትቀርብ ዋንጫን እንዲጎበኙ ከ3ሺ በላይ የስፖርት አፍቃሪዎች በኮካ ኮላ ቡድን ተመርጠዋል፡፡ የዓለም ዋጫ ከኢትዮጵያ በኋላ ጉብኝቷን የምትቀጥለው በኬንያዋ ናይሮቢ ከተማ ነው፡፡

    ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) በእያንዳንዱ የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ላይ ስለሚያበረክታቸው የተለያዩ ሽልማቶች እንዲሁም በ1978 እኤአ ከተካሄደው የዓለም ዋንጫ በብራዚል እስካስተናገደችው 20ኛው የዓለም ዋንጫ ድረስ ያሸነፏትን ሻምፒዮኖች ስፖርት አድማስ እንዲህ ያስተዋውቃቸዋል፡፡
ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) በእያንዳንዱ የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ላይ በተለያዩ የኮከብ ሽልማት ዘርፎች የክብር ዋንጫ እና ልዩ ስጦታዎችን እንደሚያበረክት ይታወቃል፡፡   እነዚህ ልዩ ልዩ ሽልማቶች ለዓለም ዋንጫው ከፍተኛ ኮከብ ግብ አግቢ፤  አስገራሚ ብቃትና ጠንካራ አቋም ለሚያሳይ ኮከብ ተጨዋችና ምርጥ ግብ ጠባቂ እንዲሁም በሌሎች የተለያዩ ዘርፎች ለተመረጡት የሚሰጡ ናቸው፡፡ ዋናዎቹ ሽልማቶች እነሱም፤ የአዲዳስ የወርቅ ጫማ፤ የአዲዳስ የወርቅ ኳስ፤ የፊፋ ስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማት፤ የምርጥ ብሔራዊ ቡድን ሽልማትና የጄሊት ምርጥ ወጣት ሽልማት ናቸው።
የአዲዳስ የወርቅ ጫማ ሽልማት
(Adidas Golden Shoe)
በዓለም ዋንጫ ላይ በኮከብ ግብ አግቢነት ለሚጨርሱ ተጫዋቾች ይሸለማል፡፡ ድሮ የወርቅ ጫማ Golden Shoe አዋርድ ተብሎ ይጠራ ነበር፡፡ ው ታላቁ የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያ አዲዳስ ስፖንሰር ካደረገው በኋላ ግን የአዳዲስ የወርቅ ጫማ ሽልማት  የሚል ስያሜ ይኖረዋል፡፡ ሽልማቱ  ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠው በ1982 እ.ኤ.አ ላይ ስፔን ባዘጋጀችው 12ኛው የዓለም  ዋንጫ ነው፡፡ ከዚህ በታች የቀረበው  ባለፉት 20 ዓለም ዋንጫዎች ኮከብ አግቢ ሆነው የጨረሱ እና የወርቅ ጫማ ተሸላሚዎች ናቸው፡፡
በ1ኛው የዓለም ዋንጫ ኡራጋይ (በ1930 እ.ኤ.አ)    በ8 ጎሎች    ጉሌርሞ ስታብል (አርጀንቲና)
በ2ኛው የዓለም ዋንጫ ጣሊያን (1934 እ.ኤ.አ) በ4 ጎሎች 4 ተጨዋቾች ኤድመንድ ኮነን (ጀርመን) ኦልድሪች ኔችድሊ (ቼኮስሎቫኪያ) ኦንጀሌ ሺያቮ (ጣሊያን)
በ3ኛው የዓለም ዋንጫ ፈረንሳይ (1938 እ.ኤ.አ) በ8 ጎሎች ሊዮናዲስ (ብራዚል)
በ4ኛው የዓለም ዋንጫ ጣሊያን ብራዚል (1950 እ.ኤ.አ) በ9 ጎሎች  አዲሜይር (ብራዚል)
በ5ኛው የዓለም ዋንጫ ስዊዘርላንድ (1954 እ.ኤ.አ)  በ11 ጎሎች ሳንዶር ኮሲስ (ሃንጋሪ)    
በ6ኛው የዓለም ዋንጫ ስዊድን (በ1958 እ.ኤ.አ) በ13 ጎሎች ጀስት ፎንታይኔ (ፈረንሳይ)    
በ7ኛው የዓለም ዋንጫ ቺሊ (በ1962 እ.ኤ.አ)  በእኩል 4 ጎሎች ጋሪንቻ (ብራዚል)፤ ሊዮኔል ቫንቼዝ (ቺሊ)፤ ድራገን ጀርኮቪች (ዩጎዝላቪያ) ፤ ቫልንቲን ኢቫኖብ (ሶቭዬት ዩኒዬን)እና ፍሎርያን አልበርት (ሀንጋሪ)
በ8ኛው የዓለም ዋንጫ እንግሊዝ (በ1966 እ.ኤ.አ) በ9 ጎሎች ዩዞብዩ (ፖርቱጋል)
በ9ኛው የዓለም ዋንጫ ሜክሲኮ (በ1970  እ.ኤ.አ) በ10 ጎሎች  ገርድ ሙለር  (ምዕራብ ጀርመን)
በ10ኛው የዓለም ዋንጫ ቺሊ  (በ1974 እ.ኤ.አ) በ7 ጎሎች ግራዜጎሬዝ  ላቶ (ፖላንድ)
በ11ኛው የዓለም ዋንጫ አርጀንቲና በ1978 እኤአ በ6 ጎሎች ማርዬ ኬም ፕስ (አርጀንቲና )
ከላይ የተዘረዘሩት ሽልማቱ በአዲዳስ ስፖንሰር ከመሆኑ በፊት በፊፋ ኮከብ ግብ አግቢ የተባሉት ናቸው፡፡
በ12ኛው የዓለም ዋንጫ  ስፔን (በ1982 እ.ኤ.አ) ፓውሎ ሮሲ (ጣሊያን)
በ13ኛው የዓለም ዋንጫ  ሜክሲኮ (በ1986 እ.ኤ.አ)  ማራዶና (አርጀንቲና)
በ14ኛው የዓለም ዋንጫ  ጣሊያን (በ1990 እ.ኤ.አ) በ6 ጎሎች  ሳልቫቶሬ ስኪላቺ (ጣሊያን)
በ15ኛው የዓለም ዋንጫ  አሜሪካ (በ1994 እ.ኤ.አ) በ6 ጎሎች   ሂርስቶ  ስቶችኮቭ  (ቡልጋርያ ) እና  ኦሌግ ሳሌንኮ (ራሽያ)    
በ16ኛው የዓለም ዋንጫ  ፈረንሳይ (በ1998 እ.ኤ.አ) )በ6 ጎሎች   ዳቮር ሱከር (ክሮሺያ)    
በ17ኛው የዓለም ዋንጫ  ደቡብ ኮርያና ጃፓን  (በ2002 እ.ኤ.አ) በ8 ጎሎች ሮናልዶ (ብራዚል)
በ18ኛው የዓለም ዋንጫ  ጀርመን  (በ2006 እ.ኤ.አ) በ5 ጎሎች ሚሮስላቭ ክሎስ (ጀርመን)
በ19ኛው የዓለም ዋንጫ  ደቡብ አፍሪካ  (በ2010 እ.ኤ.አ) በ5 ጎሎች ቶማስ ሙለር (ጀርመን)
በ20ኛው የዓለም ዋንጫ  ብራዚል   (በ20014 እ.ኤ.አ) በ6 ጎሎች ጄምስ ሮድሪጌዝ  (ኮሎምቢያ)
የአዳዲስ የወርቅ ኳስ ሽልማት
(Adidas Golden Ball ward)
የአዳዲስ የወርቅ ኳስ ሽልማት የተጀመረው በ1982 እ.ኤ.አ ከተደረገው የዓለም ዋንጫ አንስቶ ነው፡፡ በምርጫው መሰረት ከፍተኛ ድምፅ ያገኘ ተጫዋች የውድድር ኮከብ ተጫዋች ተብሎ የአዲዳስ የወርቅ ኳስ ሽልማትን ይወስዳል፡፡
በ12ኛው የዓለም ዋንጫ  ስፔን (በ1982 እ.ኤ.አ) ፓውሎ ሮሲ (ጣሊያን)
በ13ኛው የዓለም ዋንጫ  ሜክሲኮ (በ1986 እ.ኤ.አ)  ዲያጎ ማራዶና (አርጀንቲና)
በ14ኛው የዓለም ዋንጫ  ጣሊያን (በ1990 እ.ኤ.አ) ሳልቫቶሬ ስኪላቺ (ጣሊያን)
በ15ኛው የዓለም ዋንጫ  አሜሪካ (በ1994 እ.ኤ.አ) ሮማርዮ ዴ ሱዛ ፋሪያ (ብራዚል)    
በ16ኛው የዓለም ዋንጫ  ፈረንሳይ (በ1998 እ.ኤ.አ) ሮናልዶ ሊውስ ናዛሪዮ (ብራዚል)    
በ17ኛው የዓለም ዋንጫ  ደቡብ ኮርያና ጃፓን  (በ2002 እ.ኤ.አ) ኦሊቨር ካን (ጀርመን)
በ18ኛው የዓለም ዋንጫ  ጀርመን (በ2006 እ.ኤ.አ) ዚነዲን ዚዳን (ፈረንሳይ)
በ19ኛው የዓለም ዋንጫ  ደቡብ አፍሪካ  (በ2010 እ.ኤ.አ) ዲያጎ ፎርላን  (ኡራጋይ)
በ20ኛው የዓለም ዋንጫ  ብራዚል   (በ2014 እ.ኤ.አ) ሊዮኔል ሜሲ  (አርጀንቲና)
የዓለም ዋንጫ ምርጥ ቡድን
(Most Entertaining Team)
ፊፋ በዓለም ዋንጫ ምርጥ ብቃ እና አዝናኝ ጨዋታ ላሳዩ ቡድኖች  ሽልማት መስጠት የጀመረው በ1994 እኤአ በ15ኛው የ ዓለም በአሜሪካ ሲካሄድ ነው፡፡ በምርጫው የስፖርት ቤተሰቡ በሰፊው ተሳታፊ ይሆንበታል፡፡
በ15ኛው የዓለም ዋንጫ  አሜሪካ (በ1994 እ.ኤ.አ)  ብራዚል
በ16ኛው የዓለም ዋንጫ  ፈረንሳይ (በ1998 እ.ኤ.አ) ፈረንሳይ    
በ17ኛው የዓለም ዋንጫ  ደቡብ ኮርያና ጃፓን  (በ2002 እ.ኤ.አ) ደቡብ ኮርያ
በ18ኛው የዓለም ዋንጫ  ጀርመን  (በ2006 እ.ኤ.አ) ፖርቱጋል
በ19ኛው የዓለም ዋንጫ  ደቡብ አፍሪካ  (በ2010 እ.ኤ.አ) Sፔን
በ20ኛው የዓለም ዋንጫ  ብራዚል   (በ2014 እ.ኤ.አ) ጀርመን
የወርቅ ጓንት ሽልማት
በዓለም ዋንጫ በኮከብ በረኝነት ለሚመረጠው ተጨዋች የሚበረከት ነው፡፡ ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር የሽልማት ስነስርዓቱን በአሜሪካ አዘጋጅነት በተካሄደው 15ኛ የዓለም ዋንጫ ላይ ሲያስተዋወቀው  በታዋቂው ራሽያዊ በረኛ ሌቭ ያሺን መታሰቢያነት ‹‹የሌቭ ያሺን አዋርድ›› በሚል ነበር፡፡ ጀርመን እስካስተናገደችው 18ኛው የዓለም ዋንጫ ‹‹የሌቭ ያሺን አዋርድ››  ተካሂዶ ተቋርጧል፡፡ የወርቅ ጓንት ተብሎ የሽልማት ስነስርዓቱ በ2010 እና በ2014 እኤአ ተካሂዷል፡፡ ለሽልማቱ የሚበቃን በረኛ የሚመርጠው የፊፋ የቴክኒክ ቡድን ነው፡፡ ከ1938 እስከ 1990 እኤአ ድረስ በተካሄዱ ዓለም ዋንጫዎች ግብ ጠባቂ የውድድሩ ኮከከብ ተብሎ ይመረጥ ነበር፡፡
በ1ኛው የዓለም ዋንጫ ኡራጋይ (በ1930 እ.ኤ.አ)    ኤነሪኮ ባሌስትሮ ከኡራጋይ
በ2ኛው የዓለም ዋንጫ ጣሊያን (1934 እ.ኤ.አ) ሪካርዶ ዛሞራ ከስፔን
በ3ኛው የዓለም ዋንጫ ፈረንሳይ (1938 እ.ኤ.አ) ፍራንቲሴክ ፕላኔንካ ከቼኮስሎቫኪያ
በ4ኛው የዓለም ዋንጫ ጣሊያን ብራዚል (1950 እ.ኤ.አ) ሮክ ማስፖሊ ከኡራጋይ
በ5ኛው የዓለም ዋንጫ ስዊዘርላንድ (1954 እ.ኤ.አ)  ጋይዩላ ግሮስኪስ ከሃንጋሪ
በ6ኛው የዓለም ዋንጫ ስዊድን (በ1958 እ.ኤ.አ) ሃሪ ግሬግ ከሰሜን አየርላንድ
በ7ኛው የዓለም ዋንጫ ቺሊ (በ1962 እ.ኤ.አ)  ቪሊያም ሽርጆፍ ከቼኮስሎቫኪያ
በ8ኛው የዓለም ዋንጫ እንግሊዝ (በ1966 እ.ኤ.አ) ጎርደን ባንክስ ከእንግሊዝ
በ9ኛው  የዓለም ዋንጫ ሜክሲኮ (በ1970  እ.ኤ.አ) ላዲስሎ ማሲርኩዌዝ ከኡራጋይ
በ10ኛው የዓለም ዋንጫ ምዕራብ ጀርመን  (በ1974 እ.ኤ.አ) ሴፕ ሜየር ከጀርመን
በ11ኛው የዓለም ዋንጫ አርጀንቲና በ1978 እኤአ ኡባልዶ ፊሎል ከአርጀንቲና
በ12ኛው የዓለም ዋንጫ  ስፔን (በ1982 እ.ኤ.አ) ዲኖ ዞፍ ከጣሊያን
በ13ኛው የዓለም ዋንጫ  ሜክሲኮ (በ1986 እ.ኤ.አ)  ጂን ማርዬ ቢታፍ ከቤልጅዬም
በ14ኛው የዓለም ዋንጫ  ጣሊያን (በ1990 እ.ኤ.አ) በ6 ጎሎች  ሉዊስ ጋቤሎ ከኮስታሪካና ሰርጂዮ ጎይኮቻ ከአርጀንቲና
ከላይ የተዘረዘሩት ሽልማቱ ‹‹የሌቭ ያሺን አዋርድ›› ከመባሉ በፊት በፊፋ ኮከብ በረኞች የተባሉ ናቸው፡፡
በ15ኛው የዓለም ዋንጫ  አሜሪካ (በ1994 እ.ኤ.አ) ማይክል ፕሩድሆሜ ከቤልጅዬም
በ16ኛው የዓለም ዋንጫ  ፈረንሳይ (በ1998 እ.ኤ.አ)  ፋቢያን ባርቴዝ ከፈረንሳይ
በ17ኛው የዓለም ዋንጫ  ደቡብ ኮርያና ጃፓን  (በ2002 እ.ኤ.አ) ኦሊቨር ካን ከጀርመን
በ18ኛው የዓለም ዋንጫ  ጀርመን  (በ2006 እ.ኤ.አ) ጂያንሉጂ ቡፎን ከጣሊያን
የወርቅ ጓንት ተሸላሚዎች
በ19ኛው የዓለም ዋንጫ  ደቡብ አፍሪካ  (በ2010 እ.ኤ.አ) ኤከር ካስያስ ከስፔን
በ20ኛው የዓለም ዋንጫ  ብራዚል   (በ20014 እ.ኤ.አ) ማኑዌል ኑዌር ከጀርመን
የጂሌት ምርጥ ወጣት ተጫዋች ሽልማት (Gillete Best Young player award)
ከ1958 እስከ 2002 እኤአ በተካሄዱ የዓለም ዋንጫዎች ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር የውድድሩን ወጣት ተጨዋቾች ከኢንተርኔት በሚሰበስበው ድምፅ መነሻነት ይመርጥ ነበር፡፡
በ2006 እኤአ ጀርመን ካስተናገደችው  18ኛው ዓለም ዋንጫ ጀምሮ ደግሞ የጂሌት ምርጥ ወጣት ተጨዋች ሽልማት ተብሎ እየተበረከተ ነው፡፡  በዓለም ዋንጫው  ዕድሜው ከ21 ዓመታት በታች ሆኖ አስደናቂ አቋም ላሳየ ወጣት ተጫዋች ይበረከታል፡፡
በ6ኛው የዓለም ዋንጫ ስዊድን (በ1958 እ.ኤ.አ) በ17 ዓመቱ ፔሌ ከብራዚል
በ7ኛው የዓለም ዋንጫ ቺሊ (በ1962 እ.ኤ.አ)  በ20 ዓመቱ ፍሎራን አልበርት ከሃንጋሪ
በ8ኛው የዓለም ዋንጫ እንግሊዝ (በ1966 እ.ኤ.አ) በ20 ዓመቱ ፍራንዝ ቤከንባወር ከጀርመን
በ9ኛው  የዓለም ዋንጫ ሜክሲኮ (በ1970  እ.ኤ.አ) በ21 ዓመቱ ቲዮፊሎ ኩብሊያስ ከፔሩ
በ10ኛው የዓለም ዋንጫ ምዕራብ ጀርመን  (በ1974 እ.ኤ.አ) በ20 ዓመቱ ውልዳይ ዛሙዳ ከፖላንድ
በ11ኛው የዓለም ዋንጫ አርጀንቲና (በ1978 እኤአ) በ20 ዓመቱ አንቶኒዮ ካባሪኒ ከጣሊያን
በ12ኛው የዓለም ዋንጫ  ስፔን (በ1982 እ.ኤ.አ) በ21 ዓመቱ ማኑዌል አሞሮስ ከፈረንሳይ
በ13ኛው የዓለም ዋንጫ  ሜክሲኮ (በ1986 እ.ኤ.አ)  በ20 ዓመቱ ኢንዞ ሺፎ ከቤልጅዬም
በ14ኛው የዓለም ዋንጫ  ጣሊያን (በ1990 እ.ኤ.አ) በ21 ዓመቱ ሮበርት ፐሮዜንስኪ ከዩጎስላቪያ
በ15ኛው የዓለም ዋንጫ  አሜሪካ (በ1994 እ.ኤ.አ) በ21 ዓመቱ ማርክ ኦቨርማስ ከሆላንድ
በ16ኛው የዓለም ዋንጫ  ፈረንሳይ (በ1998 እ.ኤ.አ) በ18 ዓመቱ ከእንግሊዝ ማይክል ኦዌን
በ17ኛው የዓለም ዋንጫ  ደቡብ ኮርያና ጃፓን  (በ2002 እ.ኤ.አ) በ20 ዓመቱ ለንደን ዶኖቫን ከአሜሪካ
በ18ኛው የዓለም ዋንጫ  ጀርመን  (በ2006 እ.ኤ.አ) በ21 ዓመቱ ሉካስ ፖዶልስኪ ከጀርመን
 በ19ኛው የዓለም ዋንጫ  ደቡብ አፍሪካ  (በ2010 እ.ኤ.አ) በ20 ዓመቱ ቶማስ ሙለር ከጀርመን
በ20ኛው የዓለም ዋንጫ  ብራዚል   (በ20014 እ.ኤ.አ) በ21 ዓመቱ ፖል ፖግባ ከፈረንሳይ

Read 3740 times