Saturday, 24 February 2018 12:29

“ተንሳፋፊ ጀበናዎች” የስዕል አውደ ርዕይ ተከፈተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   ለአንድ ወር ለዕይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል

    በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ጥበብ ት/ቤት መምህር የሆነው የሰዓሊ ሮቤል ተመስገን ስራዎች ለእይታ የቀረቡበት “ተንሳፋፊ ጀበናዎች” የተሰኘ የስዕል አውደ ርዕይ ከትላንት በስቲያ ሐሙስ ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንዲቃ አርት ጋለሪ ተከፈተ፡፡ በአውደ ርዕዩ ላይ የቀረቡት ሥራዎች፣ ሰዓሊው ከዚህ በፊት ጥናት ባደረገበት የአድባርና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉ የጀበና እና የስኒ ስዕሎች ናቸው ተብሏል፡፡ አውደ ርዕዩ ለቀጣዩ አንድ ወር ለተመልካች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ ፡
ሰዓሊና መምህር ሮቤል ተመስገን የመጀመሪያ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ሁለተኛ ዲግሪውን ኖርዌይ ከሚገኝ የስነ-ጥበብ ት/ቤት ያገኘ ሲሆን እስከዛሬ ከ50 በላይ የስዕል ኤግዚቢሽኖችን በአፍሪካ፣ በአውሮፓና አሜሪካ እንዳቀረበ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 2217 times