Saturday, 17 February 2018 13:59

አዲሱ ደረስ፤ ኢሶግ

Written by  አዲሱ ደረስ፤ ኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

 የኦፕሬሽን ወሊድ በተረዐዶ፤ በመንግስትና በግል ሆሰፒታሎች

    የኢትዮጲያ የጽነስና ማህጸን ማህበር (ኢሶግ) የ26ኛ አመታዊ ጉባኤውን ባከናወነበት ወቅት ከቀረቡ የጥናት ውጤቶች መካከል የቀዶ ጥገና ወሊድ በተረዐዶ፤ በመንግስትና በግል ሆሰፒታሎች መካከል ያለውን ልዩነት ያሳየውና በፕፌሰር ሉክማን ዩሱፍ የቀረበው ይገኝበታል፡፡ ጥናቱ በጅማሬው በወሊድ ዙሪያ በማበረሰቡ ዘንድ እየታየ የመጣውን ለውጥ በመዳሰስ ይጀምራል።
ጥናቱ እየታዩ ነው ካላቸው ለውጦች መካከል እርግዝናን እና ወሊድን በህክምና መከታተል፤ የምጥ ፍራቻ አየጨመረ መምጣት፤ በህክምና ባለሞያዎች ዘንድ ክስን የመፍራትና ምንም አይነት የተለየ ሁኔታ የሚታይበትን እርግዝና ያለማስተናገድ የሚሉትን ዳስሶ አልፏል።
በተጨማሪም በቀዶ ህክምና የሚደረግ  ወሊድ ለህጻኑ የተሸለ የስነልቦና ጫና አለው የሚል እምነት ስለመኖሩ፤ ለህክምና ባለሞያውም የተመቸ ስለመሆኑ፤ እንዲሁም የልደት ቀንን ተከትሎ እድላኛ ልጅ ነው የሚለውን ባህላዊ እምነት አኳያ ድጋፍ ስለማግኘቱ ያትታል፡፡ ጥናቱ በተጨማሪም የቀዶ ህክምና ወሊድ እየጨመረ መምጣቱን እና በብልት በኩል የሚደረግ ወሊድ እየቀነሰ ስለመምጣቱ ይጠቅሳል፡፡
የቀዶ ህክምና ወሊድ በተጨማሪም በህክምና የትምህርት ተቋማት ውስጥ በመንግስት ከፍተኛ ደረጃ አገልግሎቱ እየተሰጠ ሲሆን አንድ ጊዜ በኦፕሬሽን የወለዱ ወላጆች ለሁለተኛ ጊዜም በቀዶ ህክምና የመውለድ እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ በጥናቱ ተጠቅሷል፡፡
በወላጆች ጥያቄ መሰረት ተደርጎ ብቻ  የሚደረግ የቀዶ ህክምና ወሊድ (ያውም ኦፕሬሽኑን ለማድረግ የሚያስገድዱ የህክምና ምክኒያቶቸች ሳይኖሩ) እየጨመረ ለመጣው በኦፕሬሽን የሚደረግ ወሊድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉንም ይጠቅሳል፡፡
በግል ተቋማት የሚደረጉ ወሊዶች በቀዶ ህክምና የመደረግ ከፍተኛ እድል እንዳላቸው እንዲሁም በግል ተቋማት የሚደረጉት ወሊዶች በስራ ሰዐት የመደረግ እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን ጥናቱ ያሳያል፡፡ በነዚህ ተቋማት የሚደረጉ ወሊዶች በቀዶ ህክምና የመሆን እድላቸው ከመጨመሩም በላይ ከስራ ሰዐት የሚደረጉ ኦፕሽኖች ወላዶችን ለተጨማ የኢኮኖሚ ወጪ እየዳረገጋቸው እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡
ጥናቱ በማጠቃለያውም በቀዶ ህክምና የሚደረጉ ወሊዶች ምናልባትም በግል ተቋማት በሚሰጡ አገልግሎቶች ምክኒያት እየተስፋፋ እንደመጣ ገምቶ፤ በግል ተቋማት ለቀዶ ህክምና የሚበጀተው በጀት ከፍተኛ መሆን አገልግሎቱን ከማስፋፈቱም በላይ ተጠቃሚው ላይ የኢኮኖሚ ጫና ሳይፈጥር እንዳልቀረ ይገምታል፡፡ በቀዶ ህክምና የሚደረጉ ወሊዶችን ተከትለው የወላጆችን እና የጨቅላዎችን ጤንነት በቅርበት መከታተል እንደሚገባ ይመክራል፡፡
ጥናቱ በተጨማሪም በብልት በኩል የሚደረግ ወሊድ ተፈጥሯዊ እና ሊበረታታ የሚገባ መሆኑን እንዲሁም አስገደዳጅ ከሆኑ የህክምና/ የጤና ሁኔታዎች ከሌሉ በስተቀር የቀዶ ህክምና ወሊድ ሊበረታታ እንደማይገባ ይሞግታል፡፡
በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ጥናቶች መደረግ እንደሚገባቸው፤ በጉዳዩም ላይ ብሄራ መግባባት እንዲኖር እና በቀዶ ህክምና ለሚደረጉ ወሊዶችም ግልጽ መመሪያዎች ሊኖሩ አንደሚገባ ይመክራል፡፡ በክልሎች ለሚደረጉ የቀዶ ህክምናዎችም አስፈላጊው የኢንፌክሸን መከላከያዎች እና የማደንዘዣ አቅርቦት ሊኖር እንደሚገባም ይጠቁማል፡፡
ተጠቃሚዎች ሊተማመኑበት የሚችሉት አይነት፤ በዋጋም  ተመጣጣኝ የሆነ እና ሁሉን አቀፍ የነብሰጡሮች እንክብካቤ አገልግሎት ሊኖር እንደሚገባ ለባሞያዎችም የህግ ተጤቂነት ፍራቻ አገልግሎቱን ከመስጠት እንዳያግዳቸው አስፈላጊው ግንዛቤ ማስጨበጫ ሊሰጥ እንደሚገባም ይጠቁማል፡፡
በተጨማሪም በብልት የሚደረግ ወሊድ ፍራቻ ካለ የሚክር አገልግሎትን መጠየቅ እንደሚገባ፤ የቀዶ ህክምና ወሊድ የሚደረግ ከሆነ፤ከዚህ በፊት የቀዶ ህክምና ወሊድ ተደርጎ ከሆነ፤ እና ጽንሱ ተፈጥሯዊ መዛባት እንዳለበት ከታወቀ ወላጆች ቀዶ ህክምናውን አዎንታዊ እና አሉታዊ ጎኖች በደንምብ ተረድተው ውሳኔ እንዲወስዱ አጥብቆ ይመክራል፡፡

--------------------------------------------------------

Read 1832 times