Saturday, 20 January 2018 13:09

“የትዳር ክትባት” መፅሐፍ ለገበያ ቀረበ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)

 በመጋቢ ዳኛቸው ሀይሉ የተዘጋጀው “የትዳር ክትባት” የተሰኘ መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡
መፅሐፉ በአሁኑ ወቅት የማህበረሰቡ አሳሳቢ ችግር በሆነው የጋብቻና ፍቺ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን ሰዎች ለጋብቻ መሰረት ከሆነው የእጮኝነት አጀማመር አንስቶ ያለውን ሂደት እንዴት መምራት እንዳለባቸው ግንዛቤ የሚያስጨብጥ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
“የትዳር ክትባት” ባለፈው ታህሳስ 26 ቀን 2010 ዓ.ም በሒልተን ሆቴል የተመረቀ ሲሆን በ122 ገፆች ተቀንብቦ፣ በ50 ብር ለሽያጭ  ቀርቧል፡፡

Read 1983 times