Saturday, 20 January 2018 13:07

ዲጄ ዊሽና አፍሮቢት ላውንጅ በአዲስ መልክ ተጣመሩ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   በከተማችን ብዙ ትልልቅ ኮንሰርቶችና ባዛሮች ላይ ሙዚቃዎችን በማቅረብ እውቅናን ያተረፈው ዲጄ ዊሽና አፍሮቢት ላውንጅ፤ደንበኞቻቸውን በላቀ ሁኔታ ለማዝናናት በአዲስ መልክና በአዲስ ቦታ ተጣመሩ፡፡ አፍሮ ቢት ላውንጅ ከዚህ ቀደም ከነበረበት ብሌን ህንፃ፣ሚሊኒየም አዳራሽ ጀርባ ወደሚገኝ ህንጻ የተዛወረ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በሚያምር የክለብ ዲዛይን፣ በምቹ መቀመጫዎች፣ በቪአይፒ ክፍሎችና በዘመናዊ የባር አደረጃጀት የአገልግሎት አሰጣጡን እንዳሳደገ ተጠቁሟል፡፡
አፍሮቢት ላውንጅና ዲጄ ዊሽ በጥምረት የሚሰጡት አገልግሎት ከትናንት በስቲያ ሐሙስ በተካሄደ የመክፈቻ ሥነሥርዓት በይፋ የተጀመረ ሲሆን እንደ አዲስ የተደራጀው ክለብ፣የዘመኑ ቴክኖሎጂ ያፈራቸው ሳውንድ ሲስተሞች፣ መብራቶች፣ የቪዲዮ ስክሪኖችና ሌሎችም ዘመናዊ መሳሪያዎች እንደተሟሉለት አፍሮቢት ላውንጅ ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫ አስታውቋል። አፍሮ ቢት ላውንጅ 150 ደንበኞችን በአንድ ጊዜ የማስተናገድ አቅም እንዳለው ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ከዲጄ ዊሽ ጋር በመሆን ደንቦኞቹን ለማዝናናት ዝግጁ ሆኖ እየጠበቀ ነው ተብሏል፡፡   

Read 878 times