በጋዜጠኛ ግሩም ተበጀ የተሰናዳው “ግሩም የዓለማችን ምርጥ ታሪኮች” መፅሐፍ ሰሞኑን ገበያ ላይ ውሏል፡፡ በመፅሐፉ ውስጥ ግለ ታሪኮች፣ አስደናቂ ታሪኮች፣ ሳይንስ፣ ሥነ ልቦና፣ መሳጭ አጫጭር ታሪኮች፣ መጣጥፎችና ሌሎችም ቁም ነገር አዘል ታሪኮች መካተታቸው ታውቋል፡፡
አብዛኞቹ ታሪኮችም በፎቶግራፎች ታጅበው የቀረቡ ናቸው፡፡ መፅሐፉ በ254 ገጾች የተመጠነ ሲሆን ለአገር ውስጥ በ70 ብር፣ለውጭ አገራት በ15 ዶላር ይሸጣል፡፡