78ኛው ዙር “ግጥም በጃዝ” የኪነ ጥበብ ምሽት የፊታችን ረቡዕ በራስ ሆቴል አዳራሽ ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ ይካሄዳል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ገጣሚና ጋዜጠኛ ነቢይ መኮንን፣ ሚካኤል ሽፈራው፣ ገዛኸኝ ፀጋው፣ በሀይሉ ገ/እግዚአብሔርና ምህረት ከበደ ግጥም፣ ወግና ዲስኩር የሚያቀርቡ ሲሆን በዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ ደራሲነት የተፃፈ አጭር ተውኔት በአርቲስት ሽመልስ አበራና እታፈራሁ መብራቱ ይተወናል ተብሏል፡፡