Saturday, 06 January 2018 13:04

ለነፍሰ ጡር እናቶች በሚጠቅሙ ምግቦች ላይ ያተኮረ መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በምግብ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ባገኙት ቴዎድሮስ ግርማ የተዘጋጀውና “የምግብ ንጥረ ነገር ፍላጎትና መልካም የአኗኗር ዘይቤ፡- ለነፍሰ ጡርና ለሚያጠቡ እናቶች” የተሰኘ መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡
መፅሐፉ በዋናነት ነፍሰ ጡር ሴቶችም ሆነ የሚያጠቡ እናቶች ለራሳቸውም ሆነ ለሚያጠቡትና ለፀነሱት ፅንስ ጠቃሚ የሆኑ የምግብ ንጥረ ነገሮችን በአግባቡ በመጠቀም፣ እንዴት ጤናማ የአኗኗር ዘዴን መከተል እንደሚችሉ ያስተምራል፡፡ በ85 ገፆች የተመጠነው መፅሐፉ፤ ለአገር ውስጥ በ100 ብር እና ለውጭ አገር በ20 ዶላር ለሽያጭ ቀርቧል፡፡

Read 1404 times