Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 21 April 2012 16:15

የትራፊክ መብራትና የብር ኖቶቻችን

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የብሮቻችን ነገር ወረቀት እየሆነብን ከተቸገርን ከራረምን፡፡ አምና ስናማርር ዘንድሮ ይብሣል፡፡ አይታወቅም ከርሞ ደግሞ ይለይለትና እናርፋለን፡፡

አምና ቡና በሚጠጣበት ዘንድሮ ሻይ አይጠጣም፤ አምና ጥብስ የሚበላበት ዘንድ የሽሮ ዋጋ ሆኗል!  …ምንም እንኳ ጡር ፈርተን “የባሰ አታምጣ” ብንልም… የድህነት ፏፏቴ ቁልቁል እየደፈጠጠን ስለሆነ ከዚህ የባሰ ምን እንሆናለን ለማለት ትንሽ የቀረን ይመስላል፡፡ ግን የበደለን ፈጣሪ አይመሥለኝም፡፡ ፈጣሪ ዝናብ ሰጠ፣ ፀሐይ ሰጠ፣ በተረፈ ሰው መስኖ ጨመረ፣ ማዳበርያ አመጣ፡፡ ምርት አደገ እየተባለ ተለፈፈ፡፡ “አደግን!” አለን መንግስት፡፡ እኛ ስናድግ አናውቅም እንዴ? ወይስ ሌሎች ያደጉ ክፍሎች አሉ? ግራ ገባን እኮ! የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች ምን እንደሚሉ ባላውቅም ምናባዊ ዕድገት ይኖር ይሆን?

ወደ ባሰ ምሬት ሣልገባ ስለ ብር ኖቶቻችን ሣሥብ ብልጭ ያለችልኝን ከትራፊክ መብራት ምልክቶች ጋር አያይዤ ላቅርብ፡፡

አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የትራፊክ መብራት አለ፡፡ ብሮቻችንም እንዲሁ ይመስላሉ፡፡ የመቶ ብር ኖት አረንጓዴ፣ የሃምሳ ብር ኖት ቢጫ፣ የአስር ብር ኖት፣ ቀይ ናቸው፡፡ ታዲያ ትርጉማቸውን ሣሠላው ከትራፊኩ መብራት ጋር አንድ ሆኖ ቁጭ አለ፡፡

ብዙ ቦታ ሲገቡ መቶ ብር ከያዙ በአማካይ የይለፍ ምልክት ያያሉ፣ ባለሃምሳ ሲይዙ ደግሞ “ተጠንቀቁ፤ አይሞላቀቁ!” ይልዎታል፡፡ ባለ አስር ቀይዋን ከያዙ “ቁም!” ይልዎታል! ምክንያቱም አሥር ብር አታራምድም! አይገርምም! ብሔራዊ ባንክና መንገድ ትራንስፖርት ተማክረውብን ይሆን እንዴ?

 

 

Read 2801 times Last modified on Saturday, 21 April 2012 16:17