Tuesday, 02 January 2018 10:22

“ድርና ማግ” የሥነ-ፅሁፍ ምሽት ሊጀመር ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

በባህልና ኪነ-ጥበብ ላይ አተኩሮ በየወሩ የሚካሄድ “ድርና ማግ” የስነ-ፅሁፍ ምሽት የፊታችን ሀሙስ መገናኛ በሚገኘው አፋራንሲስ ኢንተርናሽናል ሆቴል ከቀኑ 11፡00 ይጀምራል፡፡
በመጀመሪያው የሥነ ፅሁፍ ምሽት ሰዓሊና መምህር እሸቱ ጥሩነህና የሙዚቃ ሃያሲው ሰርፀፍሬ ስብሀት ዲስኩር የሚያቀርቡ ሲሆን አርቲስት ስዩም ተፈራ፣ ገጣሚያኑ ረድኤት ተረፈ፣ ሰይፉ ወርቁ፣ ሙሉቀን ሰለሞንና ንዋይ ከፍያለው የግጥም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡ በተጨማሪም በሀይሉ ገ/እግዚአብሔርና አርቲስት ሀገረገወይን አሰፋ ወግ የሚያቀርቡ ሲሆን ምሽቱ በመሶብ ባህላዊ ባንድ እንደሚታጀብና አዝናኝ ሲትኮም ድራማም የዝግጅቱ አካል እንደሚሆን ታውቋል፡፡

Read 2124 times