Monday, 25 December 2017 00:00

በባልደራስ ልዩ የገና በዓል የመዝናኛ ፕሮግራም ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ገቢው ሙሉ በሙሉ በ”ራዕይ የህፃናትና ቤተሰብ ልማት ማህበር” በነፃ ለሚማሩና ለሚመገቡ ከ380 በላይ ህፃናት ድጋፍ የሚውል ልዩ የገና በዓል የመዝናኛ ፕሮግራም ዛሬ ይካሄዳል፡፡
በባልደራስ አዳራሽ ግቢ ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በሚካሄደው በዚህ ልዩ የወላጆችና የልጆች የገና የመዝናኛ ፕሮግራም፤ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በልጆች ክፍለ ጊዜ የምታስተዋውቀው ኢትዮጵያ፤ በስፍራው በመገኘት ለህፃናቱ የተለያዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞች ታቀርባለች ተብሏል፡፡
ገቢው የድሃ ቤተሰብ ልጆችን ለመመገብና ለማስተማር በሚውለው በዚህ ልዩ የመዝናኛ ፕሮግራም ላይ በ”ራዕይ የህፃናት የቤተሰብ ልማት ማህበር” የሚማሩ ህፃናት፣ የገና መዝሙር የሚያቀርቡ መሆኑን የፕሮግራሙ አዘጋጅ “አሪፍ ኮሚዩኒኬሽን እና ኮንስልታንሲ ኃ. የተ.የግል ማህበር” ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፍሬወይኒ ግደይ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ በዕለቱም ወላጆች ልጆቻቸውን ይዘው በሥፍራው በመገኘት ለህፃናቱ የተዘጋጁትን የተለያዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞች እንዲመለከቱና የኢኮኖሚ አቅማቸው ደካማ የሆኑ ወላጆች ልጆችን ለመደገፍ በሚደረገው ጥረት፣ የድርሻቸውን እንዲያበረክቱ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Read 1844 times Last modified on Saturday, 23 December 2017 14:30