Print this page
Saturday, 23 December 2017 10:48

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጋምቤላ ለህዝብ ያስገነባውን ጤና ጣቢያ አስመረቀ

Written by 
Rate this item
(3 votes)

 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጋምቤላ ክልል ከ9 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባውን ጤና ጣቢያ ያስመረቀ ሲሆን ተመሣሣይ ጤና ጣቢያዎችን በሁሉም ክልሎች እየገነባ መሆኑን አስታውቋል፡
 ባንኩ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት በየአመቱ ከፍተኛ በጀት መድቦ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በተለይ በጤና፣ በትምህርት፣ በአከባቢ ጥበቃ፣ በአካል ጉዳተኞች በአረጋዊያን፣ በህፃናት እና ሴቶች ዙሪያ የድጋፍ እንቅስቃሴዎች እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ከሠሞኑ የዚህ ፕሮጀክት አካል የሆነውንና በጋምቤላ ክልል በኢታንግ ልዩ ወረዳ በሌር ቀበሌ ያስገነባውን ጤና ጣቢያ የክልሉ ምክትል ርዕሠ መስተዳደርና የፐብሊክ ሠርቪስና የሠው ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሰናይ አኩኑር በተገኙበት አስመርቋል፡፡
ምክትል ርዕሠ መስተዳደሩም በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ባንኩ ለክልሉ ህዝብ አጋርነት ማሣየቱን አመስግነው ህዝቡ ጤና ጣቢያውን በአግባቡ እንዲጠቀምበት አሣስበዋል፡፡
በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት የባንኩ የኮሚኒኬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ በልሁ ታከለ በበኩላቸው በቀጣይም ባንኩ በጤናው ዘርፍ ተመሣሣይ ስራዎችን እንደሚያከናውን አስታውቀዋል፡፡
በአሁኑ ወቅትም በዘጠኙም ክልሎች በጠቅላላው ከ66 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ተመሣሣይ ጤና ጣቢያዎች እየስገነባ መሆኑን አቶ በልሁ አስታውቀዋል፡፡

Read 2011 times
Administrator

Latest from Administrator