Print this page
Saturday, 23 December 2017 10:33

ፊሊንትስቶን በልደታ የገነባውን የገበያ ማዕከል አስመረቀ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)


   ፍሊንትስቶን ኢንጅነሪንግ አ.ማ ለተለያዩ የንግድ አገልግሎቶች በልደታ የገነባውን ባለ 7 ፎቅ የ“ልደታ - መርካቶ የገበያ ማዕከል ህንፃ ትናንት አስመርቆ ለደንበኞቹ አስረከበ፡፡
ይህ ባለ 7 ፎቅ ህንፃ መደበኛ መብራት በሚጠፋበት ወቅት የሶላር ኤሌክትሪክ ኃይልን የሚጠቀም መሆኑ ተነገረለት ሲሆን ከህንፃው ስር ባለ ሁለት ወለል የመኪና ማቆሚያ ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡  ህንፃው በጠቅላላው 380 የንግድ ሱቆች ያሉት ሲሆን ከ1-3ኛው ወለል ያሉ ሱቆች ለአዋቂ አልባሳትና ጫማዎች መሸጫዎች ብቻ፣ 4ኛ ወለል የመዋቢያዎችና ጌጣጌጦች መሸጫ ሱቆች፣ 5ኛ ወለል ኤሌክትሮኒክስ መሸጫ ሱቆች፣ 6ኛ ፎቅ የህፃናት አልባሳት መሸጫ ሱቆች እንዲኖሩት ታስቦ ለደንበኞች ሽያጭ መከናወኑ ተገልጿል፡፡
7ኛ ፎቅም የሲኒማ እና ጌም ዞን አገልግሎት ይኖረዋል ተብሏል፡፡
የዚህ ህንፃ ዲዛይን በተለየ ሁኔታ በስፔናዊ አርክቴክት መሰራቱንና የምድር ቤቱም ለዕቃ ማከማቻ አገልግሎት ይውላል ተብሏል፡፡  

Read 2947 times
Administrator

Latest from Administrator