Saturday, 16 December 2017 00:00

የኮክ ስቱዲዮ አፍሪካ የመዝጊያ ኮንሰርት ዛሬ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በዘንድሮው የኮክ ስቱዲዮ አፍሪካ የተሳተፉት ታዋቂዎቹ የአገራችን ድምፃዊያን ለዝግጅቱ መዝጊያ የሚሆን ደማቅ የሙዚቃ ኮንሰርት ዛሬ ከምሽቱ 12፡30 ጀምሮ በጊዮን ሆቴል እንደሚያቀርቡ ተገለፀ፡፡
በዘንድሮው የኮክ ስቱዲዮ አፍሪካ ሳሚ ዳን፣ አስገኘሁ አሸኮ (አስጌ ዴን ዳሾ)፣ ቤቲ ጂ፣ ጃኖ ባንድ እና ዳዊት ነጋ (ወዛመይ) የተሳተፉ ሲሆን በዛሬው የመዝጊያ ኮንሰርት ላይ ከዳዊት ነጋ በስተቀር ሁሉም ተሳታፊዎች የሙዚቃ ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡
እስከ እኩለ ሌሊት በሚዘልቀው በዚህ ኮንሰርት ላይ ሳሚ ዳን “ዘውድ ባንድ” በተሰኘው የራሱ ባንድ ሲታጀብ፣ ጃኖ ባንድም በራሱ ባንድ ደምቆ እንደሚያመሽ የተገለፀ ሲሆን የመግቢያ ክፍያ እንደሌለውና በግብዣ ካርድ ብቻ መታደም እንደሚቻል ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 1469 times