Sunday, 10 December 2017 00:00

ኦሪጅናል ያልሆኑ የአይፎን ቻርጀሮች እሳት ሊፈጥሩ ይችላሉ ተባለ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በህገወጥ መንገድ በሚመረቱ፣ ጥራት በሌላቸውና ኦሪጅናል ባልሆኑ የአይፎን ቻርጀሮችና በሌሎች ቻርጀሮች የአይፎን የሞባይል ስልኮችን ቻርጅ ማድረግ የእሳት አደጋን፣ በኤሌክትሪክ የመያዝና ከፍተኛ የመቁሰል አደጋን የማስከተል እድላቸው እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ዘ ቴሌግራፍ ዘግቧል፡፡
መሰል ቻርጀሮች ምንም እንኳን በአነስተኛ ዋጋ ቢገዙም ለአደጋ የማጋለጥ እድላቸው እጅግ ከፍተኛ መሆኑን በእንግሊዝ አገር በሰራሁት የደህንነት ፍተሻ ጥናት ደርሼበታለሁ ያለው ኤሌክትሪካል ሴፍቲ ፈርስት የተባለ የአገሪቱ ተቋም፤ ጥናት ካደረግኩባቸው ቻርጀሮች መካከል 98 በመቶው እጅግ አደገኛ እንደሆኑ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
ጥናት ከተደረገባቸው አይፎንን ቻርጅ ማድረግ የሚችሉ ሌሎች 50 አይነት ቻርጀሮች ውስጥ ከአንዱ በስተቀር ሌሎቹ የተለያዩ አይነት የደህንነት መስፈርቶችን ያላሟሉ ሆነው መገኘታቸውንም ተቋሙ አስታውቋል፡፡ አይፎንን ቻርጅ በሚያደርጉ ሌሎች 400 አይነት ቻርጀሮች ላይ በአሜሪካ ባለፈው አመት በተሰራ ሌላ ተመሳሳይ ጥናት፣ ቻርጀሮቹ የመበላሸትና አደጋ የማስከተል እድላቸው 99 በመቶ ያህል መሆኑ መረጋገጡንም ዘገባው አስታውሷል፡፡

Read 1466 times