ውድ እግዚአብሔር፡-
ቃየል እና አቤል የየራሳቸው ክፍል ቢኖራቸው ኖሮ እርስ በርስ አይጋደሉም ነበር፡፡ ለእኔና ለወንድሜ ለላሬ ይሄ ነገር ሰርቶልናል፡፡
-ዴቭ-
ውድ እግዚአብሔር፡-
እግዚአብሔር መሆንህን እንዴት አወቅህ?
-ሳሚ-
ውድ እግዚአብሔር፡-
እባክህ የፈረስ ግልገል ላክልኝ፡፡ ከዚህ ቀደም ምንም ነገር ጠይቄህ አላውቅም፡፡ መዝገብህን መመልከት ትችላለህ፡፡
-ጆሴፍ-
ውድ እግዚአብሔር፡-
እባክህ ሚኪን ወደ ሌላ ሰፈር ውሰደው፡፡ እባክህ … እባክህ!!
-ኤርሚ-
ውድ እግዚአብሔር፡-
አንተ እንዴት ልትፈጠር ቻልክ?
-ሳራ-
ውድ እግዚአብሔር፡-
እኔ ጥሩ ወይም መጥፎ ስሆን ታውቃለህ እንዴ? ወይስ የገና አባት ብቻ ናቸው የሚያውቁት?
-ሮዚ-