Saturday, 18 November 2017 12:31

ንግድ ባንክ 10ኛውን ዙር የ“ይጠቀሙ ይሸለሙ” አሸናፊዎች ሸለመ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 1ኛ ባለዕድል 15 ሰዎች የሚይዝ ሚኒባስ ተሸልሟል
                 
    የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግና የባንኩን ተጠቃሚዎች ለማበረታታት አቅዶ የጀመረው 10ኛው የ“ይጠቀሙ ይሸለሙ” የሽልማት ስነ-ስርዓት ከትላንት በስቲያ ረፋድ ላይ በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አዳራሽ የተካሄደ ሲሆን 1ኛ ባለዕድል 15 ሰዎች የሚይዝ ሚኒባስ ተሸልሟል፡፡
በዚህ ሽልማት ላይ እድለኛ የሆኑት ከውጭ የሚላክላቸውን ገንዘብ በባንኩ በኩል የወሰዱ፣ የውጭ ምንዛሬ የመነዘሩና ተያያዥ የባንክ አገልግሎቶችን የተጠቀሙ እንደሆኑ በእጣ አወጣጥ ስነ - ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የባንኩ ኃላፊዎች ገልፀዋል፡፡
የአንደኛ እጣ ባለ እድል ከ10-15 ሰው የሚጭን ሚኒባስ፣ ሁለተኛ እጣ 16 ባለዕድሎች እያንዳንዳቸው ሞተር ብስክሌት፣ ሶስተኛ እጣ 32 ባለዕድሎች እያንዳንዳቸው ስማርት የሞባይል ቀፎ ተሸልመዋል፡፡ ባንኩ በአሁኑ ወቅት 1235 ቅርንጫፎቹን በመላ አገሪቱ መክፈቱን፣ የደንበኞቹን ብዛትም ወደ 16.5 ሚ. ማሳደጉን የባንኩ የኮሚዩኒኬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ በልሁ ታደሰ ገልፀዋል፡፡

Read 1598 times