Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 14 April 2012 12:25

የአውሮፓ ሻምፒዮኖችን ለመለየት ደርቢዎች ወሳኝ ሆነዋል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በአውሮፓ 5 ታላላቅ ሊጎች የ2011/12 የውድድር ዘመን ሊጠናቀቅ የቀረው የወር እድሜ ሲሆን በየሃገሩ 1ኛና 2ኛ ደረጃ በያዙ ክለቦች የሻምፒዮናነት ትንቅንቅ ተሟሙቋል፡፡ በ5ቱም ትልልቅ ሊጎች ዋንጫውን ለማንሳት ከሚደረጉት ቀሪ ግጥሚያዎች በተለይ ደርቢዎች ወሳኝነት ይኖራቸዋል፡፡ በእንግሊዝ  ሲቲ በሜዳው ኢትሃድ ዩናይትድን የሚያስተናግድበት የማንችስተር ደርቢና በስታድዮ በርናባኦ የሚካሄደው የሪያል ማድሪድ እና የባርሴሎና የኤልክላሲኮ ፍጥጫ  በፕሪሚዬር ሊግና በላሊጋው ማን ዋንጫ ይበላል ለሚለው  ጥያቄ ምላሽ የሚኖራቸው ጨዋታዎች ናቸው፡፡ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ማንችስተር ዩናይትድና ማን ሲቲ፤ በስፔን ላሊጋ ሪያል ማድሪድና  ባርሴሎና፤ በጀርመን ቡንደስ ሊጋ ዶርትመንድና ባየር ሙኒክ፤ በጣሊያን ሴሪኤ ኤሲ ሚላንና ጁቬንትስ፤ በፈረንሳይ ሞንትፕሌርና ፓሪስ ሴንትዠርመን፤  የየሊጋቸው ሻምፒዮን የመሆን እድል እንደያዙ ናቸው፡፡

በ20ኛው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ከወር በፊት መሪነቱን ያስነጠቀው ማንችስተር ሲቲ  በቅርብ ተቀናቃኙ ማን ዩናይትድ በ5 ነጥብ ተበልጦ ለዋንጫው እንዳደፈጠ ነው፡፡ ማንችስተር ሲቲ ከ44 ዓመታት በኋላ የመጀመርያውን የሻምፒዮናነት ክብር ለማንሳት ያለው እድል አልተሰናከለም፡፡ ማንዩናይትድ በበኩሉ በውድድሩ ታሪክ 20ኛውን የሊግ ዋንጫ በማንሳት ከፍተኛውን የውጤት ክብረወሰን ለመያዝ ያነጣጥራል፡፡ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ልክ የዛሬ ወር የሚገባደድ ሲሆን  እስከ 33ኛ ሳምንት በተደረጉ  327 ጨዋታዎች 914 ጎሎች ገብተዋል፡፡ የሊጉን ደረጃ ሰንጠረዥ በ79 ነጥብ እና በ50 የግብ ክፍያ የሚመራው ማን ዩናይትድ ሲሆን ማን ሲቲው በ74 ነጥብና በ53 የግብ ክፍያ ይከተለዋል፡፡ ሮበን ቫንፒርሲ 27 ጎሎችን በማስመዝገብ ኮከብ ግብ አግቢነቱን አየመራ ሲሆን ሩኒ ከማን ዩናይትድ በ22 ሰርጂዮ አጉዌሮ ከማን ሲቲ በ19 ጎሎች ይከተሉታል፡፡81ኛው የስፔን ላሊጋ ላይ ሪያል ማድሪድ መሪነቱን እየገፋ ቢሆንም  ባርሴሎና የነጥብ ልዩነቱን በ4 በማጥበብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ነው፡፡ ማድሪድ ባርሴሎና አስከትሎ ላሊጋውን መምራቱ ከ4 ዓመት በዃላ ለመጀመርያ ጊዜ ሻምፒዮን ሊሆን  ይችላል፡፡በላሊጋው እስከ 32ኛው ሳምንት 317 ጨዋታዎች ተካሂደው 879 ጎሎች ከመረብ አርፈዋል፡፡ ለኮከብ ግብ አግቢ በቀረበው የፒቺቺ አዋርድ ሮናልዶ በ40 ጎሎቹ እየገሰገሰ ሲሆን ሊዮኔል ሜሲ በ39 ጎሎች እየተከተለው ነው፡፡ ከሳምንት በኋላ በሳንቲያጎ በርናባኦ የሚከናወነው የኤልክላሲኮ ጨዋታ የሻምፒዮናነቱ ፉክክር የሚወስን እንደሚሆንም ተጠብቋል፡፡ ላሊጋውን ሪያል ማድሪድ በ82 ነጥብ እየመራ ሲሆን ባርሴሎና በ78 ነጥብ እየተከተለው ከወር በኋላ ይገባደዳል፡፡

በ49ኛው የጀርመን ቦንደስ ሊጋ ቦርስያ ዶርትመንድ ሰሞኑን ባየር ሙኒክን ከረታ በኋላ በ6ነጥብ ልዩነት መሪነቱን በማስፋት 69 ነጥብ ይዞ አንደኛነቱን እንደተቆጣጠረ ነው፡፡ ሁለተኛ የሆነው ባየር ሙኒክ ተፎካካሪነቱ አልቀነሰም፡፡ ቦንደስ ሊጋው ሊጠናቀቅ 3 ሳምንታት ሲቀሩት እሰከ 30ኛው ሳምንት 270 ጨዋታዎች ተደርገው 774 ጎሎች ተመዝግበዋል፡፡ ኮከብ ግብ አግቢነቱን የባየር ሙኒኩ ማርዮ ጎሜዝ በ25 ጎሎች እየመራ ነው፡፡ 80ኛው የጣሊያን ሴሪኤን ባለፈው ሳምንት በድጋሚ መምራት የጀመረው ኤሲ ሚላን  ነው፡፡ ጁቬንትስ  ሁለተኛ ደረጃን በቅርብ ይዞታል፡፡ የጣሊያን ሴሪኤ ከወር በኋላ የሚገባደድ ሲሆን ባለፈው ሰሞን ብቻ መሪነቱን ኤሲ ሚላንና ጁቬንትስ ተፈራርቀውበት የዋንጫ ፉክክራቸውን አጋግለውታል፡፡ እስከ 32ኛው ሳምንት 319 ጨዋታዎች ተደርገው 816 ጎሎች ከመረብ አርፈዋል፡፡  ጁቬንትስ ሊጉን በ68 ነጥቦች እየመራ ሲሆን ኤሲ ሚላን በ67 ዱካውን ይዞታል፡፡

በኮከብ ግብ አግቢነቱ ፉክክር የኤሲ ሚላኑ ኢብራሞቪች በ23 ጎሎች መሪ ነው፡፡

በ74ኛው የፈረንሳይ ሊግ 1 ሰሞኑን ማርሴይን ካሸነፈ በኋላ ፓሪስ ሴንትዠርመን መምራት ጀምሯል፡፡ በፈረንሳይ ሊግ 1 የውድድር ዘመኑ ሊጠናቀቅ 5 ሳምንታት የሚቀሩ ሲሆን ሞንትፕሌየር በ66 ነጥብ በመምራት ላይ ነው፡፡ ፓሪስሴንት ዠርመን በ63 ነጥብ ይከተለዋል፡፡ በሊጉ በ31 ሳምንታት በተደረጉ 310 ጨዋታዎች 767 ጎሎች ተቆጥረዋል፡፡

 

 

Read 2936 times Last modified on Saturday, 14 April 2012 12:33