Print this page
Sunday, 05 November 2017 00:00

የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት መካነ ቅርስ አደጋ ተጋርጦበታል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(10 votes)

*መካነ ቅርሱን ከውድመት ለማዳን 1ቢ.ብር ገደማ ያስፈልጋል
*ፓትርያርኩ፤ ለጠ/ሚኒስትሩ ደብዳቤ ፅፈዋል

ለዘመናት የአገር ገፅታን ሲገነባ የኖረው የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት መካነ ቅርስ ህልውናው አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን አፋጣኝ ጥገና ካልተደረገለት በቅርቡ ወደ ፍርስራሽነት ሊቀየር እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን  ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በበኩላቸው፤ የጉዳዩን አሳሳቢነት በመግለጽ ለጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ደብዳቤ መጻፋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡   
የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት መካነ ቅርስን ከውድመት ለማዳን ወደ 1 ቢሊዮን ብር ገደማ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡  
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የቅርስ ጥናት ጥበቃ ኃላፊ ቀሲስ ሰለሞን ቶልቻ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ቅርሱ ከፍተኛ አደጋ የተጋረጠበት መሆኑን ጠቁመው፣ሥር ነቀል ጥገናና እንክብካቤ ካልተደረገለት፣ ከትውልዱ እጅ ወጥቶ ታሪክ ብቻ ሆኖ ሊቀር እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡  
“ከ800 አመት በላይ እድሜ ያስቆጠረው የላሊበላ መካነ ቅርስ፤እርጅና፣በአካባቢው ያሉ ዕጽዋት የሚፈጥሩት ብስባሽና በላዩ ላይ የተቀመጠው ጥላ አደጋ ጋርጠውበታል”ብለዋል፤ቀሲስ ሰለሞን፡፡
ከ8 ዓመት በፊት የአውሮፓ ህብረት ለቅርሱ ግዙፍ የብረት መጠለያ (shelter) አሰርቶለት የነበረ ቢሆንም መጠለያው ጊዜውን ጠብቆ ባለመጠገኑ ወይም ባለመቀየሩ የተያያዘበት አለት እየተሰነጠቀ መሆኑንና ይህም በአብያተ ክርስቲያኑ ላይ ወድቆ ወድመት ያደርሳል የሚል ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩን ሃላፊው ገልጸዋል፡፡ ጥላው የአገልግሎት ጊዜው ካለፈ 5 ዓመት እንደሆነው የጠቆሙት ቀሲስ ሰለሞን፤ አሁን ይህ ጥላ ለቅርሱ ስጋት ሆኗል ብለዋል፡፡ ይህን ጉዳይ አርኪዮሎጂስቶች፣ አርክቴክቶች፣ የቅርስ ባለሙያዎችና ምሁራን ተመልክተው፣ ጥላው መነሣት እንዳለበት፣ ካልተነሳ ግን አደጋው የከፋ እንደሚሆን ምክረ ሀሳብ ማቅረባቸውን ጠቁመዋል። ለቅርሱ የሚደረገው ጥገናም ይህን አደጋ የጋረጠውን መጠለያ በከፍተኛ ጥንቃቄ ከማንሳት መጀመር እንዳለበት የጠቆሙት ሃላፊው፤ ቤተ ክህነትም ጥላው እንዲነሳ ወስናለች ብለዋል፡፡
ጥገናው የፖለቲካ ውሳኔ ያስፈልገዋል ያሉት ቀሲስ ሰሎሞን፤ቅዱስ ሲኖዶስ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የጉዳዩን አሳሳቢነት በመግለፅ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲያመለክቱ ተደርጓል ብለዋል፡፡ ይህ መካነ ቅርስ የሃገር ገጽታን ሲገነባ የኖረ ነው የሚሉት ኃላፊው፤ ጥገና በማድረግ ሂደት ውስጥም ሃይማኖት ሳይለይ ሁሉም ሊሳተፍበት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ “ቅርሱ በዚህ ትውልድ ፊት ከእጃችን ሊወጣ ተቃርቧል፤ መገናኛ ብዙኃንም ለጉዳዩ ትኩረት እየሰጡ አለመሆኑ አሳሳቢ ነው” ብለዋል-ቀሲስ ሰለሞን፡፡

Read 3883 times