Saturday, 04 November 2017 12:55

ዳሽን ባንክ ባለ 21 ፎቅ የዋና መ/ቤት ሕንፃ ዛሬ ያስመርቃል

Written by  መንግሥቱ አበበ
Rate this item
(1 Vote)

በአዲስ ምዕራፍ ጉዞ የጀመረው ዳሽን ባንክ፤ ከብሔራዊ ባንክ ፊት ለፊት በአንድ ቢሊዮን ብር ወጪ ያስገነባውን የዋና መ/ቤት ዘመናዊ ሕንፃ፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለ ሥልጣናትና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ዛሬ ያስመርቃል፡፡
3 ቤዝመንትን ጨምሮ 21 ፎቅ ያለው ይህ ዘመናዊ ሕንፃ፤ የሠራተኞች መዝናኛ፤ መመገቢያ፣ የጤና እንክብካቤና የሕፃናት ማቆያ ሲኖረው፣ 2 የቪአይፒ፣ 5 የሰውና 1 የዕቃ በአጠቃላይ 8 ሊፍቶች (አሳንሰሮች)፣ 170 መኪኖችን መያዝ የሚችል የመኪና ማቆሚያ፣ በእያንዳንዱ ፎቅ ላይ የተለያየ መጠን ያላቸው የስብሰባ ክፍሎች፣ ጂምናዝየም (ላውንጅ፣ ስቲምና ሳውና)፣ 120 መቀመጫዎች ያሉት የሠራተኞች ካፍቴሪያ፣ የጨቅላ ሕፃናት ማቆያ ክፍሎች፣ በእያንዳንዱ ፎቅ የምግብ ማዘጋጃ ክፍል፣ እንዲሁም ሠራተኞች የሚታከሙበት ክሊኒክ እንዳለው ታውቋል፡፡

Read 2854 times