Saturday, 04 November 2017 11:56

“የማማ ስር መኝታ” የግጥም መድበል ነገ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

የገጣሚ ሄርሜላ ገ/እግዚአብሔር “የማማ ስር መኝታ” የተሰኘ የግጥም ስብስብ መፅሀፍ ነገ ከረፋዱ 4፡00 ጀምሮ አምስት ኪሎ በሚገኘው ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አዳራሽ ይመረቃል፡፡
በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ 50 ግጥሞችን ያካተተው መፅሀፉ በ62 ገፆች ተቀንብቦ በ30 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ወጣትና አንጋፋ ገጣሚያን ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ። ገጣሚ ሄርሜላ የመፅሀፉን ገቢ ሙሉ ለሙሉ “ተስፋ ብርሀን” ለተሰኘ የበጎ አድራጎት ማህበር መለገሷም ታውቋል፡፡

Read 1661 times