Sunday, 05 November 2017 00:00

የፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ መፅሐፍ ማክሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 የፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ “ስውሩና ያልተነገረው የአይሁዳዊያንና የኢትዮጵያዊን ታሪክ” መፅሐፍ  የፊታችን ማክሰኞ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በብሄራዊ ቴአትር አዳራሽ ይመረቃል፡፡ በዕለቱ ፕሮፌሰሩ ስለመፅሐፉ አጠቃላይ ይዘት ማብራሪያ የሚሰጡበት መልዕክት እንደሚልኩ የተገለፀ ሲሆን መጋቢ ሀዲስ እሸቱ ዓለማየሁ ደግሞ መፅሀፉ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ምን ጨመረ? በሚለው ዙሪያ አስተያየት ይሰጣሉ ተብሏል፡፡
 የታሪክ ምሁሩ አቶ ቢኒያም አሊ በበኩላቸው፤ በመፅሐፉ ላይ ሂስ እንደሚሰጡም ታውቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም ቅኔና ግጥም፣ በላይ በቀለ ወያ ግጥም የሚያቀርቡ ሲሆን ደራሲና ጋዜጠኛ በሀይሉ ገ/እግዚአብሔር ወግ እንደሚያቀርብ ተገልጿል፡፡ መፅሐፉ ቀደም ሲል በእንግሊዝኛና በእብራይስጥ አሁን ደግሞ በአማርኛ ቋንቋ ተፅፎ ለአንባቢ የቀረበ ሲሆን በተለይ በእብራይስጥ ቋንቋ መፃፉን ተከትሎ ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ከእስራኤሉ ሊኩድ ፓርቲ መሪ አድናቆትና የእውቅና ወረቀት ማግኘታቸው ተጠቁሟል፡፡

Read 982 times