Saturday, 28 October 2017 10:51

“አቤሴሎም” መፅሀፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

በእውነተኛ ታሪኮች ላይ የተመሰረተውና በዶ/ር ደሳለው ካሳሁን የተፃፈው “አቤሴሎም” የተሰኘ መፅሀፍ ዛሬ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በብሄራዊ ቤተ-መፅሀፍትና ቤተ-መዛግብት አዳራሽ ይመረቃል፡፡
ደራሲው ባለፈው ወር ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ በህክምና በዶክትሬት ዲግሪ የተመረቀ ሲሆን በስድስት አመት የግቢ ቆይታው፣ ከፃፋቸው ስድስት ረጃጅም ልቦለዶች “አቤሴሎም” ቀድሞ የህትመት ብርሀን ለማግኘት እንደቻለ ታውቋል፡፡ የዩኒቨርሲቲውን የህክምና ሁኔታ በጥልቀት የሚዳስሰው መፅሀፉ፤ ዛሬ በምርቃቱ ላይ ለዳሰሳ እንደሚያቀርብም ታውቋል፡፡ በ206 ገፆች የተመጠነው መፅሀፉ፤ በ75 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 2339 times