Saturday, 28 October 2017 10:50

“ግጥም ለትውልድ” የግጥም መድበል ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)

በገጣሚ ወ/ሮ አስራት ጥላሁን የተሰናዳውና በሴት ልጅ ጥቃት፣ በልጅ አስተዳደግና በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ በርካታ ግጥሞችን የያዘው “ግጥም ለትውልድ” የተሰኘ መፅሀፍ፣ ዛሬ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ ቢጂአይ ኢትዮጵያ መዝናኛ ጀርባ በሚገኘው ሶሊስ ኢንተርናሽናል ሆቴል ይመረቃል፡፡ በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የሴት ደራሲያን ማህበር ፕሬዚዳንት እምወድሽ በቀለ በክብር እንግድነት የሚገኙ ሲሆን እሳቸውን ጨምሮ ሌሎች አንጋፋና ወጣት ገጣሚያን ከመፅሀፉ የተመረጡ ግጥሞችንና የራሳቸውን ስራዎች ያቀርባሉ ተብሏል፡፡ ገቢው ለአካል ጉዳተኞች ይውላል የተባለው መፅሀፉ፣ በ84 ገፆች ተቀንብቦ፣ በ50 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 2649 times