ቶሞካ ቤተ-ሥዕል ማሳያ 24ኛውን “ጥበብና ጊዜ! ትላንት ዛሬና ነገ” የተሰኘ የስዕል ትርኢት፣ ትላንት ምሽት 12፡00 ከፈተ፡፡ በዚህ የስዕል ትርኢት፤ መውደድ ዳኛቸው እና አማኑኤል ወንደሰን የተባሉ የሁለት ወጣት ሰዓሊያን ስራ በጋራ ለእይታ የበቃበት እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ወጣቶቹ በስራዎቻቸው በሰው ልጅ የወጣትነት የጎልማሳነትና በእርጅና ዘመን ያለን የሰውነት ሁኔታ የሚያሳየውን ገፅታና በአጠቃላይ በሰው ልጅ መልክ ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ትላንት የተከፈተው ይህ የስዕል ትርኢት፤ እስከ ቀጣዩ ጥር ሶስት ለእይታ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይም
ታውቋል፡፡