Saturday, 30 September 2017 15:13

ባንኮክ በ20.2 ሚ. ሰዎች በመጎብኘት የአለም መሪነቱን ተቆጣጥራለች

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በየዓመቱ በዓለማቀፍ ቱሪስቶች በብዛት የተጎበኙ የዓለማችን ከተሞችን ደረጃ ይፋ የሚያደርገው ማስተርካርድ የተባለው ኩባንያ፣ ከሰሞኑም የ2017 ዝርዝሩን ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ በዓመቱ 20.2 ሚሊዮን ዓለማቀፍ ጎብኝዎች ያፈራቺው የታይላንድ መዲና ባንኮክ በአንደኛነት ተቀምጣለች፡፡የእንግሊዟ ርዕሰ መዲና ለንደን በ20 ሚሊዮን፣የፈረንሳዩዋ ፓሪስ በ16.1 ሚሊዮን፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትሷ ዱባይ በ16 ሚሊዮን፣ ሲንጋፖር በ13.45 ሚሊዮን ዓለማቀፍ ጎብኝዎች፣በቅደም ተከተላቸው እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ መያዛቸውን ኩባንያው
ባወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡የጃፓን መዲና ቶክዮ፣ የደቡብ ኮርያዋ ሴኡል፣የአሜሪካዋ ኒውዮርክ፣ የማሌዢያዋ ኳላላ ላምፑር እና ሆንግ ኮንግ እስከ አስረኛ ያለውን ደረጃ መያዛቸውንም ኩባንያው ለዘጠነኛ ጊዜ ይፋ ባደረገው አመታዊ መረጃው አመልክቷል፡፡4.8 ሚሊዮን ዓለማቀፍ ቱሪስቶች የጎበኟት የደቡብ አፍሪካዋ ጁሃንስበርግ፣ ከአፍሪካ ከተሞች ቀዳሚነቱን ስትይዝ፣ በዓለማቀፍ ደረጃ ደግሞ 30ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

Read 2065 times