Monday, 25 September 2017 12:17

የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር ሕንፃ የመሠረት ድንጋይ በመስቀል በዓል ይቀመጣል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

በክረምቱ ሲሠለጥኑ የነበሩ የስነ ጽሑፍ ሠልጣኞች በዕለቱ ይመረቃሉ

ኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር ጽ/ቤትና የፓን አፍሪካ ደራስያን ማዕከል እንደሚሆን የተነገረለት ህንፃ የመሰረት ድንጋይ፤ በበዓ፤ መስቀል እንደሚቀመጥ፣ የደራስያን ማህበር በጽ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ አስታወቀ፡፡ በዕለቱ ማኅበሩ፣ በስነ-ፅሁፍ፣ በሂስ አቀራረብ፣ በስነ ግጥምና ተያያዥ ጉዳዮች ያሰለጠናቸውን ከ40 በላይ ሰልጣኞች እንደሚያስመርቅ ተገልጿል፡፡ሲኤምሲ ሚካኤል አጠገብ የከተማው አስተዳደር
ከሊዝ ነፃ ለማህበሩ በሰጠው 3 ሺህ ካ.ሜ ቦታ ላይ በሚካሄደው የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ ስነ-ስርዓት፣የኢፌድሪ ም/ል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡ለግንባታው፣ ከ80 ሚ. ብር በላይ እንደሚያስፈልግ የገለፁት አመራሮቹ፤ ከተለያዩ ግለሰቦችና ተቋማት
ድጋፍ የሚያሰባስብ የምሁራንና ደራስያን ኮሚቴ እንደሚቋቋምም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Read 856 times