እንደ እርስዋ ገለፃ አሁን እየተሰበሰቡ ያሉት መፃሕፍት ቃሊቲ ለሚገኘው ማረሚያ ቤት እንደሚሰጡና ማረሚያ ቤቱ በራሱ ማጓጓዣ መፃሕፍቱን ለታራሚዎቹ አብያተ መፃሕፍት ለማድረስ ቃል ገብቷል፡፡ ከጥበብ ኢትዮጵያ ጋር በመሆን ለሚቀርበው ዝግጅት ጃፋር መፃሕፍት መደብር፣ ቢጂአይ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር፣ እና ኬር ማስታወቂያና ፕሮሞሽን እገዛ አድርገውለታል፡፡ ሰኞ ምሽት በትያትር ቤቱ ለሚቀርበው ኪነጥበባዊ ዝግጅት መግቢያ ከወትሮው የተለየ ሆኖ ታዳሚዎች መፅሐፍ እንደ ትኬት እንደሚጠቀሙም ማወቅ ተችሏል፡፡ ግጥምና ሙዚቃ፣ መጣጥፍ፣ ወግ፣ አጭር ተውኔት፣ ሥዕል፣ ቅርፃ ቅርፅ የሚቀርቡ ሲሆን ከእለቱ እንግዶች መካከልም ጌትነት እንየው፣ በቀለ መኮንን፣ ስለሺ ደምሴ፣ ዳዊት ፍሬው፣ ኤፍሬም ስዩም፣ ባንቺአየሁ ዓለሙ፣ ምልዕቲ ኪሮስ ይገኙበታል፡፡