Monday, 18 September 2017 10:55

“እስቲ ሙዚቃና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች” ሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  የደራሰ ሌሊሣ ግርማ አምስተኛ መፅሐፉ የሆነው “እስቲ ሙዚቃ እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች”፤ በቅርቡ ስራ በጀመረው በሳፋየፍ አዲስ ሆቴል፣   ሰኞ ከ11፡30 ጀምሮ ይመረቃል፡፡ በምርቃቱ ፕሮግራም ላይ ገጣሚ ነቢይ መኮንን፣ አርቲስት ተፈሪ አለሙ፣ ደራሲ አንዱአለም ተስፋዬ፣ ገጣሚ ባንቻየሁ አለሙ፣ ጋዜጠኛና ፀሐፊ ተፈሪ መኮንን እና ሌሎች ታዋቂ የጥበብ ሰዎች ስራቸውን ለታዳሚ ያቀርባሉ፡፡ በመፅሃፉ ላይ ዳሰሳ የሚቀርብ ሲሆን የተቀነጨበ ታሪክም ይነበባል ተብሏል፡፡ ሌሊሳ ለረዥም ዓመታት ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ አጭር ልብወለዶችና ወጎችን በመፃፍ ይታወቃል። ከዚህ ቀደም “የንፋሰ ህልም እና ሌሎች የምናብ
ታሪኮች”፣ “አፍሮጋዳ”፣ “መሬት - አየር - ሰማይ” እና “የሰከረ እውነታ” የተሰኙ መፅሐፍትን ለአንባቢያን ያቀረበ ቢሆንም መፅሐፍ ሲያስመርቅ ግን የአሁኑ
የመጀመሪያው ነው፡፡

Read 2410 times