Print this page
Saturday, 02 September 2017 12:52

በ300 ሚ. ብር የተገነባውን ሆቴል፤ ዓለማቀፉ ሂልተን ሊያስተዳድረው ነው

Written by  (ናፍቆት ዮሴፍ)
Rate this item
(1 Vote)

 በታፍ ቢቢ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ በ300 ሚ ብር የተገነባውን ባለ 4 ኮከብ ሆቴል፣ አለማቀፉ ሂልተን ወርልድ ዋይድ ሊያስተዳድረው ነው፡፡
የታፍ ቢቢ ቢዝነስ  መስራችና የቀድሞው የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት  አቶ ተካ አስፋው እንደገለፁት፤ ሆቴላቸው በዓለም አቀፉ ሂልተን የተመረጠው በሶስት ዋና ዋና ምክንያቶች መሆኑን ገልፀው፣ አንደኛ በዲዛይኑ፣ ሁለተኛ በተገነባበት ቦታ (ሎኬሽን) እና ከአውሮፓ ባስገባቸው ጠቅላላ የግንባታና የመገልገያ መሳሪያዎች ነው፡፡
ከ60-70 በመቶ ግንባታው የተጠናቀቀውና ቦሌ መድሀኒያለም አጠገብ የሚገኘው ሆቴሉ፤ ሂልተን አለም አቀፍ በአውሮፓና በአሜሪካ  ከሚያስተዳድራቸው “ደብልትሪ ሆቴል ባይ ሂልተን” በሚል ከሚታወቁ እውቅ በሆኑት ሆቴሎች ተሰይሞ፣ በሂልተን እንደሚተዳደር እና ታፍ ቢቢ ፒኤልሲና ሂልተን ወርልድ ዋይድ በዚሁ ጉዳይ ላይ የፊታችን ሰኞ ምሽት በሂልተን ሆቴል እንደሚፈራረሙ አቶ ተካ አስፋው ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ሆቴሉ ግንባታው ሲጠናቀቅ ከ400-500 ለሚደርሱ ሰዎች የስራ እድል እንደሚፈጥር የገለፁት የሆቴሉ ባለቤት ደረጃቸውን የጠበቁ 108 የመኝታ ክፍሎች፣ ትልቅና ዘመናዊ አዳራሽ፣ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ሬስቶራንት፣ ሶስት ባሮችና በሂልተን ዓለምአቀፍ ደረጃ 4 ሊፍቶች፣ ለጤና ተስማሚ የሆኑ ጂም ናስፓ፣ ያሉት ነው ብለዋል፡፡ ከኤርፖርት በቅርብ ርቀት ላይ የተገነባው “ደብልትሪ ሂልተን ሆቴል” በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ ደረጃ በሂልተን የሚተዳደር የመጀመሪያው ሆነ እንደሆነ ታውቋል፡፡

Read 2991 times