Saturday, 02 September 2017 11:48

መንግስት ለአዲሱ አመት ልዩ መርሃ ግብር አዘጋጀ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(10 votes)

    አዲሱን አመት በልዩ መርሃ ግብር ለመቀበል መዘጋጀቱን የገለፀው መንግስት፤ አጋጣሚው ባለፉት አስር አመታት የነበሩብንን ድክመቶችና ጥንካሬዎች ለመገምገም መልካም እድል ይፈጥራል ብሏል፡፡
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገር ሌንጮ፤ መንግስት አዲሱን የ2010 ዓ.ም ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ ለመቀበል ያወጣውን መርሃ ግብሮች በዝርዝር ባስረዱበት ወቅት፤ የመርሀ ግብሩ የመጨረሻ ቀን ላይ “የኢትዮጵያ ቀን” ይከበራል ብለዋል፡፡
መርሃ ግብሩ ከነሐሴ 27 ቀን ጀምሮ እስከ አዲስ አመት ዋዜማ ጳጉሜ 5 ቀን 2009 ዓ.ም የሚዘልቅ ሲሆን በእነዚህ ቀናት ውስጥ አስር ዋነኛ መርሃ ግብሮች መያዛቸው ታውቋል፡፡
ነሐሴ 27 ቀን የሚከበረው የእናቶችና የህፃናት ቀን ሲሆን ነሐሴ 28 የአረጋውያን ቀን ነሐሴ 29 የሰላም ቀን፣ ነሐሴ 30 የንባብ ቀን፣ ጳጉሜን 1- የአረንጋዴ ልማት ቀን፣ ጳጉሜ 2 የመከባበር ቀን፣ ጳጉሜ 3 የአገር አቀፍ ቀን፣ ጳጉሜ 4 የአንድነት ቀን እንዲሁም ጳጉሜ 5 የኢትዮጵያ ቀን ተብለው ይከበራሉ፡፡
“መጪው ዘመን የኢትዮጵያ ከፍታ ነው” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው አዲሱ ዓመት፤ ሀገሪቷ በ10 ዓመት ውስጥ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች ያስመዘገበችው ውጤት ይገመገምበታል ተብሏል፡፡
ባለፉት 10 ዓታመታት ሁለንተናዊ ለውጦች አምጥታለች ያሉት ሚኒትሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በበኩላቸው ለዚህ ውጤት መሳካት ምክንያቱ በአዲሱ ሚሊኒየም መንግስትና ህዝብ ለተሻለ እድገት ሞራል ሰንቀው መንቀሳቀሳቸው ነው ብለዋል፡፡
በመንግስት የወጣው ልዩ የበዓል አከባበር መርሃ ግብር ላይ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በአንድት እንዲሳተፍ ጥሪ የቀረበ ሲሆን ተግባራቱ በተጠቀሱት ቀናት ተከብረው የሚያልፉ ብቻ ሳይን ከአገሪቷ ርዕይ የወደፊት ተልዕኮ ጋር ተያይዞ ለወደፊትም የሚከናወኑ ናቸው ተብሏል፡፡


Read 4421 times