Saturday, 02 September 2017 11:44

ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ፣የድህረምረቃ ፕሮግራም ሊጀምር ነው

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(1 Vote)

212 ስልጣኞች ዛሬ ያስመርቃል

ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ በቀጣዩ የትምህርት ዘመን ኬኒያ ውስጥ ከሚገኘው MOI University ጋር በመተባበር፣ በድህረ ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎችን ለመቀበል መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡
ኮሌጁ በዛሬው ዕለት በትራቭልና ቱሪዝም፣ በበረራ መስተንግዶ፣ በሆቴል ኦፕሬሽን፣ በፍሮንት ኦፊስ ኦፕሬሽን፣ በትኬቲንግና ሪዘርቬሽን ያሰለጠናቸውን 212 ተማሪዎች በኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት አዳራሽ ዛሬ ያስመርቃል። ከአለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበርና እንግሊዝ አገር ከሚገኘው Institute of Commercial Management  ጋር በመተባበር ነው ያሰለጠናቸው ተብሏል፡፡
የኮሌጁ ዋና ስራ አስፈፃሚ ካፒቴን አበራ ለሚ እንደተናገሩት፤ ተመራቂዎቹ በአገራችን የሚንቀሳቀሱ የግል አየር መንገዶች፣ ሆቴሎችና የቱሪዝም ኢንዱስትሪው ያለበትን ከፍተኛ የሰለጠነ ባለሙያ እጥረት ለማስወገድ ያስችላሉ ብለዋል፡፡
የኮሌጁ ዲን አቶ ገዛኻኝ ብሩ እንደገለፁት፤ ኮሌጁ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ እየታየ የመጣውን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ዕድገት ለማገዝ የሚችሉ ባለሙያዎችን በማፍራት ረገድ እያበረከተ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው፣ የባለሙያዎቹን አቅም ይበልጥ ለማሳደግ የሚያስችል የድህረ ምርቃ ትምህርት ፕሮግራም በቀጣዩ ዓመት ይጀምራል ብለዋል፡፡

Read 1536 times