Sunday, 27 August 2017 00:00

“አላቲኖስ” መፅሐፍ ማክሰኞ ገበያ ላይ ይውላል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(4 votes)

    “ሳቄን ማን ሰረቀኝ” የግጥም መፅሐፍ ዛሬ ይመረቃል
      “የነጎድጓድ ልጆች” እና “ለምን አትቆጣም” በሚሉት መፅሐፎቹ የሚታወቀው ደራሲ ቃል ኪዳን ኃይሉ፤ “አላቲኖስ” በሚል ርዕስ ያዘጋጀው ሦስተኛ መፅሃፉ፤ የፊታችን ማክሰኞ ለገበያ እንደሚበቃ ተገለፀ፡፡
መፅሐፉ መንፈሳዊ ልቦለድ ይዘት ያለው ሲሆን፤ ጭብጡ ከኒቂያ ጉባኤ አሁን እስካለው ክርስትና የሚዳስስ ነው ተብሏል፡፡ “አላቲኖስ” በዋናነት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን “ሪሊጂዮ ፖለቲክስ” የሚዳስስ መሆኑን ደራሲው ጠቁሟል፡፡ በ292 ገፆች የተቀነበበው መፅሐፉ፤ በ80 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ደራሲው በአሁኑ ሰዓት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን የሚተላለፈው የ “ወላፈን” ድራማ ደራሲም ነው፡፡
በተመሳሳይ መኖሪያዋን ጀርመን ኮሎኝ ያደረገችው ገጣሚ ሀና ወንድምስሻ፤ “ሳቄን ማን ሰረቀኝ” የተሰኘ የግጥም መድበል ሰሞኑን ለንባብ የበቃ ሲሆን ዛሬ ጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በጁፒተር ሆቴል ይመረቃል ተብሏል፡፡
መፅሐፉ ከ30 በላይ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ ግጥሞችን ማካተቱን ገጣሚዋ ገልፃለች፡፡ በ74 ገፆች ተመጥኖ፣ በ40 ብርና በ10 ዩሮ ለገበያ የቀረበው መፅሐፉ፤ የመጀመሪያው እትም ሙሉ ሽያጭ ለመሰረት በጎ አድራጎት ድርጅት እንደሚውል ታውቋል፡፡

Read 4041 times