Saturday, 19 August 2017 13:12

5ኛው የዓመቱ የበጎ ሰው ሽልማት ነሐሴ 28 ይካሄዳል

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(1 Vote)

   • በ10 ዘርፎች 30 እጩዎች ለውድድር ቀርበዋል
                            • የውጪ አገር ዜጎች ዘርፍ ዘንድሮ ተጀምሯል
                              
      በዲያቆን ዳንኤል ክብረት የተጠነሰሰው የበጎ ሰው ሽልማት ዘንድሮ ለ5ኛ ጊዜ የፊታችን ነሐሴ 28 ቀን 2009 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡ በአስር ዘርፎች ለሚካሄደው የበጎ ሰው ሽልማት ውድድር፤ በአጠቃላይ 30 እጩዎች፣ ከእያንዳንዱ ዘርፍ 3 ግለሰቦች፣ ለውድድር መቅረባቸውን፣አሸናፊዎቹም የፊታችን ነሐሴ 28 ቀን 2009 በሚካሄደው የሽልማት ሥነሥርዓት ላይ ይፋ እንደሚደረጉ አዘጋጁ ዲያቆን ዳንኤል  ከትናንት በስቲያ ፕሮግራሙን አስመልክቶ፣ በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል በሰጠው  ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግሯል፡፡
ለውድድሩ የቀረቡት አስር ዘርፎች፡-
መንግስታዊ የሥራ ኃላፊነትን በብቃት መወጣት ዘርፍ
 አቶ ገመቹ ደቢሶ (ከዋናው ኦዲተር)
 ዶክተር መስፍን አርአያ (ከአማኑኤል ሆስፒታል- የአእምሮ ሐኪም)
አቶ ማቲዎስ አስፋው (የአዲስ አበባ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር)  
በሚዲያና ጋዜጠኝነት ዘርፍ
 ሸገር ኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ
 የጣቢያው ጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ
 የቪኦኤ ጋዜጠኛው ንጉሴ አክሊሉ
 በቅርስ ባህልና ቱሪዝም ዘርፍ
ጉዞ አድዋ፣ (ወጣቱ የአድዋን ታሪክ እንዲያስብና እንዲያስከብር በማድረግ)
አቶ ገብረእየሱስ ኃይለማርያም (የጉራጌ አካባቢ ቅርሶችንና ባህል በማጥናት፣ በመጠበቅና በመሰብሰብ)
የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቤተ መዛግብት
ሳይንስ ዘርፍ
ዶ/ር ቦጋለ ሰለሞን (የካንሰር ህመም ስፔሻሊስቱ)
ሎሬት ዶክተር ለገሠ ወልደዮሐንስ (ከዶክተር አክሊሉ ለማ ጋር በመሆን የብሊሐርዚያን መድሃኒት ያገኙ)
ኤመሪተስ ፕሮፌሰር ንጉሴ ተበጀ  (በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር)
በኪነጥበቡ (ቲያትር ዘርፍ)
ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ
ገጣሚና ፀሐፌ ተውኔት ጌትነት እንየው
አዘጋጅና ተዋናይ ዓለማየሁ ታደሰ  
በንግድና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ
ኢንጅነር ፀደቀ ይሁኔ፣ (የፍሊንስቶን ባለቤት)
 አቶ ሰለሞን ሙሉጌታ፣ (የእሽሩሩ ስልጠና ማዕከል ባለቤት)
ሸዋ ዳቦና ዱቄት ፋብሪካ
 በበጎ አድራጎት ዘርፍ
መቅደስ ዘራራው (የተቀናጀ የቤተሰብ አገልግሎት ድርጅት መስራች)
 አቶ ዳዊት ኃይሉ (የውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ባለቤት)
ሰለሞን ይልማ (በደብረዘይት ከተማ ችግረኞችን በመርዳት ላይ የሚገኝ)
በማህበራዊ ጥናት ዘርፍ
ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ (የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪ)
 ዶ/ር የራስ ወርቅ አድማሴ
ዶክተር ካሣሁን ብርሃኑ
 በመምህርነት ዘርፍ
አቶ ፍቃደ ደጀኔ (በመርሃቤቴና በአርሲ ያስተማሩ፣ በገጠር ት/ቤቶች ያሰሩ፣ ልጆችን እየረዱ ያስተማሩ)
መምህር ሰለሞን ጸደቀ (በወሎ-ቦረና ጋሞጎፋ፣ ደብረማርቆስና ወለጋ ያስተማሩ፣ በገጠር ት/ቤት ያሰሩ)
አቶ ማሞ ከበደ (በጎልማሶች ትምህርት ላይ ለውጥ ያመጡ)
ለኢትዮጵያ መልካም የሰሩ የውጪ አገር ዜጎች ዘርፍ (ዘንድሮ የተጀመረ)
ቦብ ጊልዶፍ፣ (በ1977 ተከስቶ በነበረው ድርቅ፣ ለኢትዮጵያ እርዳታ ያሰባሰበ)
 ዶ/ር ካትሪን ሐምሊን (የፌስቱላ ሆስፒታል መስራች)
ፕሮፌሰር ጃኮብ ሸኒይደር  (በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚያገለግሉ ስዊዘርላንዳዊ ሃኪም)
ከ300 በላይ ጥቆማዎችን መቀበላቸውን የገለፀው ዲያቆን ዳንኤል፤ ከጥቆማዎቹ መካከል 30ዎቹን መርጠው በእጩነት ለማቅረብ ከፍተኛ ልፋት የጠየቀ ሥራ እንደነበርም ተናግሯል፡፡ በዳኞች የሚመረጡት አስሩ ተሸላሚዎች፤ የፊታችን ነሐሴ 28 ቀን 2009 ዓ.ም በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል በሚካሄድ ሥነ ሥርዓት ይፋ እንደሚደረግም ታውቋል፡፡  

Read 1873 times