Saturday, 19 August 2017 12:47

ጅማ ዩኒቨርሲቲ፤ በአዲስ አበባ አዳዲስ ፕሮግራሞችን ማስተማር ሊጀምር ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

   ተማሪዎች በሥራ ገበታቸው ላይ እያሉ የከፍተኛ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ያደርጋል

     ጅማ ዩኒቨርሲቲ አራት የተለያዩ የትምህርት ዘርፎችን፣ በአዲስ አበባ ለማስተማር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ ዩኒቨርሲቲው በዘንድሮ ዓመት በድህረ ምረቃ ፕሮግራም ያስተማራቸውን 68 ተማሪዎች ለሶስተኛ ጊዜ አስመርቋል፡፡
ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ በሸራተን ሆቴል ባካሄደው የምርቃ ሥነ - ሥርዓት ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ፍቅሬ ለሜሳ እንደተናገሩት፤ የትምህርትን ጥራት በማስጠበቅና ብቃት ያለው የተማረ የሰው ኃይል በማፍራት ረገድ ዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ጠቁመው፣ በቀጣይም በሂውማን ኒውትሪሽን፣ በዶክተር ኦፍ ሜዲሲን፣ በአካውንቲንግና ፋይናንስ እንዲሁም በፕሮጀክት ማኔጅመንት ትምህርቶችን ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል ብለዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ኤቢኤች ሰርቪስ ከተባለው ድርጅት ጋር በመተባበር፣በአዲስ አበባ በጀመረው የድህረ ምረቃ ፕሮግራም 68 ተማሪዎችን አስተምሮ፣ሰሞኑን በማስተርስ ኦፍ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን አስመርቋል፡፡  በርካታ ተማሪዎች በሥራ ገበታቸው ላይ እያሉ የከፍተኛ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ለማድረግ ዩኒቨርሲቲው ከኤቢኤች ሰርቪስ ጋር በጀመረው በዚህ ፕሮግራም፤ እስከ አሁን 304 ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡ 

Read 2610 times